ኢሳይያስ 43:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጥንት ጀምሮ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእጄም የሚያመልጥ የለም፤ እሠራለሁ፤ ወደ ኋላስ የሚመልስ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከጥንት ጀምሮ እኔው ነኝ፤ ከእጄም ማውጣት የሚችል የለም፤ እኔ የምሠራውን ማን ማገድ ይችላል?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም አምላክ ነኝ፥ ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ ከእጄም የሚያመልጥ የለም፤ እሠራለሁ፥ የሚከለክልስ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ከጥንት ጀምሮ አምላክ ነኝ፤ ከእጄ ማንም ማንንም አያድንም፤ እኔ ያደረግኹትን መለወጥ የሚችል የለም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ ከእጄም የሚያመልጥ የለም፥ እሠራለሁ፥ የሚከለክልስ ማን ነው? |
ቅዱስ እግዚአብሔር ይህን መክሮአል፤ የእግዚአብሔርን ምክር የሚመልስ ማን ነው? የተዘረጋች እጁንስ የሚመልሳት ማን ነው?
በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እናገራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች፤ የመከርሁትንም ሁሉ አደርጋለሁ እላለሁ።
እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፤ እስከ ሽበትም ድረስ እኔ ነኝ፤ እኔ እታገሣችኋለሁ፤ እኔ ሠርቻለሁ፤ እኔም ይቅር እላለሁ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፤ እኔም አድናችኋለሁ።
ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፤ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።
ለዘለዓለም በአርያም የሚኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱሳን የሆነ፥ በቅዱሳን አድሮ የሚኖር፥ ለተዋረዱት ትዕግሥትን የሚሰጥ፥ ልባቸውም ለተቀጠቀጠ ሕይወትን የሚሰጥ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
እኔም ለኤፍሬም እንደ ነብር፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፤ እኔም ነጥቄ እሄዳለሁ፤ እወስድማለሁ፤ የሚያድናቸውም የለም።
አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።
አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፣ አቤቱ፥ ለፍርድ ሠርተኸዋል፥ ለተግሣጽም አድርገኸዋል።
በሬህ በፊትህ ይታረዳል፤ ከእርሱም አትበላም። አህያህ ከእጅህ በግድ ይወሰዳል፤ ወደ አንተም አይመለስም፤ በጎችህ ለጠላቶችህ ይሰጣሉ፤ የሚረዳህም አታገኝም።
እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገድላለሁ፤ አድንማለሁ፤ እኔ እገርፋለሁ፤ ይቅርም እላለሁ፤ ከእጄም የሚያመልጥ የለም።