እነዚህ አገልጋዮችህ ሁሉ፦ አንተ ውጣ፤ የሚከተሉህም ሕዝብ ሁሉ ከዚያች ምድር ይውጡ እያሉ ወደ እኔ ይወርዳሉ፤ ለእኔም ይሰግዳሉ፤ ከዚያም በኋላ እወጣለሁ።” ሙሴም በጽኑ ቍጣ ከፈርዖን ዘንድ ወጣ።
ኢሳይያስ 41:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ የሚቃወሙህ ሁሉ ያፍራሉ፤ ይዋረዱማል፤ እንዳልነበሩም ይሆናሉ፤ ጠላቶችህም ይጠፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ የተቈጡህ ሁሉ፣ እጅግ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም፤ የሚቋቋሙህ፣ እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ይጠፋሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፥ ይዋረዳሉም፤ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፥ ይጠፋሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንተ ላይ የተቈጡ ሁሉ ተሸንፈው ያፍራሉ፤ አንተንም ለመጒዳት የሚነሡ ጠፍተው እንዳልነበሩ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፥ ይዋረዱማል፥ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፥ ይጠፉማል። |
እነዚህ አገልጋዮችህ ሁሉ፦ አንተ ውጣ፤ የሚከተሉህም ሕዝብ ሁሉ ከዚያች ምድር ይውጡ እያሉ ወደ እኔ ይወርዳሉ፤ ለእኔም ይሰግዳሉ፤ ከዚያም በኋላ እወጣለሁ።” ሙሴም በጽኑ ቍጣ ከፈርዖን ዘንድ ወጣ።
እንዲህም ሆነ፤ እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ እስከ ውኃ ቀጅዋ ምርኮኛ በኵር ድረስ፥ በግብፅ ምድር በኵሩን ሁሉ፥ የእንስሳውንም በኵር ሁሉ መታ።
አንተ ግን ቃሌን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጥላቸዋለሁ፤ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ።
ብዙዎች አሕዛብ እንደ ብዙ ውኃ ናቸው፤ ከፏፏቴ ውስጥ በኀይል እንደሚወርድ እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ ይጮኻሉ፤ ያጠፉታልም፤ እነርሱም ከሩቅ ይወርዳሉ፤ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ፥ በነፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረው እንደ መንኰራኵር ትቢያም ይበተናሉ።
በአርኤልም ላይ የሚዋጉ፥ ኢየሩሳሌምንም የሚወጉ፥ በእርሻዋም ላይ የሚሰበሰቡ የሚያስጨንቋትም፥ የአሕዛብ ሁሉ ብልጽግና እንደሚያልም ሰው ሕልም ነው።
ሰዎች ተርበው ሌሊት በሕልማቸው ይበላሉ፤ ይጠጣሉም፤ በተነሡ ጊዜ ግን ሕልማቸው ከንቱ ነው። የተጠማ ሰውም እንደሚጠጣ ያልማል፤ በነቃም ጊዜ እንደ ተጠማ ነው፤ ነፍሱም በከንቱ ትመኛለች። ደብረ ጽዮንን የሚዋጉ የአሕዛብ ብልጽግናም እንደዚሁ ነው።
ካህናት ሆይ፥ ለኢየሩሳሌም ወደ ልቧ የሚገባ ነገርን ተናገሩ፤ ውርደቷ እንደ ተፈጸመ፥ ኀጢአቷም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች አጽናኑአት።
እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፥ “በኀያላን የተማረኩ ይወሰዳሉ፤ የጨካኞችም ብዝበዛ ያመልጣል፤ እኔም ፍርድሽን እፈርድልሻለሁ፤ ልጆችሽንም አድናለሁ።
የአስጨናቂዎችሽንም ሥጋቸውን ይበላሉ፤ እንደ ጣፋጭ ወይን ጠጅም ደማቸውን ጠጥተው ይሰክራሉ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መድኀኒትሽና ታዳጊሽ፥ የያዕቆብን ኀይል የምደግፍ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ እንዲከናወን አላደርግም፤ በአንቺ ላይ ለፍርድ የሚነሣውን ድምፅ ሁሉ ታጠፊያለሽ፤ ጠላቶችሽም ሁሉ ይፈረድባቸዋል፤ እግዚአብሔርንም ለሚያገለግሉ ርስት አላቸው፤ ጻድቃኔም ትሆኑኛላችሁ ይላል እግዚአብሔር።
እስራኤል ለእግዚአብሔር ቅዱስ ነበረ፤ የቡቃያው በኵራትም ነበረ፤ የበሉት እንደ በደለኞች ይቈጠራሉ፤ ክፉም ነገር ያገኛቸዋል፤ ይላል እግዚአብሔር።”
በዚያም ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፣ የሚሸከሙአት ሁሉ እጅግ ይቈስላሉ፣ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በላይዋ ላይ ይከማቻሉ።
እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።