ኢሳይያስ 33:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአርያም የሚኖር ቅዱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ይኖራል፤ ጽዮንም ፍርድንና ጽድቅን ተሞላች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በአርያም ተቀምጧልና ከፍ ከፍ አለ፤ ጽዮንን በጽድቅና በፍትሕ ይሞላታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ፤ ጽዮንን በፍትህና በጽድቅ ሞላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ነው! በሰማያትም ይኖራል፤ ለጽዮንም ጽድቅንና ፍትሕን ያጐናጽፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ፥ ጽዮንን በፍርድና በጽድቅ ሞላት። |
በዚያ ጊዜም ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፤ እንዲህም ብለው ተናገሩ፦ “ለእግዚአብሔር እንዘምራለን፤ በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎአልና፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።
በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፥ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ክብሩን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ አስታውሱ።
የትዕቢተኞች ሰዎች ዐይኖች ይዋረዳሉ፤ የሰዎችም ኵራት ትወድቃለች፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።
በዚያም ቀን ይህን ቅኔ በይሁዳ ምድር ይዘምራሉ፤ እነሆም፥ የጸናችና የምታድን፥ ቅጥርንና ምሽግንም የምታደርግ ከተማ አለችን።
አምላካችን እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፤ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።
ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፤ ጽዮን ሆይ፥ ኀይልሽን ልበሺ፤ አንቺም ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንቺ አያልፍምና ክብርሽን ልበሺ።
ለዘለዓለም በአርያም የሚኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱሳን የሆነ፥ በቅዱሳን አድሮ የሚኖር፥ ለተዋረዱት ትዕግሥትን የሚሰጥ፥ ልባቸውም ለተቀጠቀጠ ሕይወትን የሚሰጥ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
ምድርም ቡቃያውን እንደምታወጣ፥ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል፥ እንዲሁ ጌታ እግዚአብሔር ጽድቅንና ደስታን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ያበቅላል።
እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድም ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድን ነው?
“እነሆ ለዳዊት የጽድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥” ይላል እግዚአብሔር፤ ንጉሥ ይነግሣል፤ ያስባል፤ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።
በዘመኑም ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፤ ይህም ስም እግዚአብሔር በነቢያት ኢዮሴዴቅ ብሎ የጠራው ነው።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ምርኮአቸውን በመለስሁ ጊዜ በይሁዳ ሀገር በከተሞችዋ፦ የጽድቅ ማደሪያ ሆይ! የቅድስና ተራራ ሆይ! እግዚአብሔር ይባርክህ የሚል ነገርን እንደ ገና ይናገራሉ።
ከዚህ በኋላም መላው እስራኤል ይድናሉ፤ መጽሐፍ እንዲህ እንዳለ፥ “አዳኝ ከጽዮን ይወጣል፤ ከያዕቆብም ኀጢአትን ያስወግዳል።
እግዚአብሔር ታጋሽ በመሆኑ፥ እሺ በማለቱም እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስም የሚያምኑትን እንደሚያጸድቃቸው ዛሬ ያውቁ ዘንድ ነው።