ኢሳይያስ 26:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ሙታን ሕይወትን አያዩአትም፤ ባለ መድኀኒቶችም አያስነሡም፤ ስለዚህም አንተ አምጥተሃቸዋል፤ አጥፍተሃቸውማል፤ ወንዶቻቸውንም ሁሉ አስወግደሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ሞተዋል፤ ከእንግዲህ በሕይወት አይኖሩም፤ መንፈሳቸው ተነሥቶ አይመጣም። አንተ ቀጣሃቸው፤ አጠፋሃቸው፤ መታሰቢያቸውንም ሁሉ ደመሰስህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ሞተዋል፥ በሕይወት አይኖሩም፤ ጠፍተዋል፥ አይነሡም፤ ስለዚህ አንተ ጎብኝተሃቸዋል፤ አጥፍተሃቸውማል፤ መታሰቢያቸውንም ሁሉ እንዳልነበር አድርገሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚያ ሁሉ ሞተዋል፤ ዳግመኛም በሕይወት አይኖሩም፤ አንተም ቀጥተሃቸው ስለ ተደመሰሱ፥ ዳግመኛ አይነሡም፤ መታሰቢያቸውም ጠፍቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ ሞተዋል፥ በሕይወት አይኖሩም፥ ጠፍተዋል፥ አይነሡም፥ ስለዚህ አንተ ጎብኝተሃቸዋል አጥፍተሃቸውማል፥ መታሰቢያቸውንም ሁሉ ምን ምን አድርገሃል። |
ከዚህም በኋላ ኀጢአቱን ያስባል። እንደ ጤዛ ትነት ይጠፋል። እንደ ሥራውም ይከፈለዋል። ዐመፀኛም ሁሉ እንደ በሰበሰ ዛፍ ይሰበራል።
እግዚአብሔርም በዚያ ቀን እስራኤልን ከግብፃውያን እጅ አዳናቸው፤ እስራኤልም ግብፃውያን እንደ ሞቱ በባሕር ዳር አዩ።
ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን አንዳች አያውቁም፤ መታሰቢያቸውም ተረስቶአልና ከዚህ በኋላ ዋጋ የላቸውም።
ሙታን ይነሣሉ፤ በመቃብር ያሉም ይድናሉ። በምድርም የሚኖሩ ደስ ይላቸዋል፤ ከአንተ የሚገኝ ጠል መድኀኒታቸው ነውና፤ የኃጥኣንንም ምድር ታጠፋለህ።
ድንገትም ፈጥኖ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅ ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።
አማልክቶቻቸውንም በእሳት አቃጥለዋል፤ የእንጨትና የድንጋይ የሰው እጅ ሥራም ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።
እነርሱም፥ “ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ጠይቁ” ባሉአችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን? ወይስ ለሕያዋን ሲሉ ሙታንን ይጠይቃሉን?
በዚያም የማያዩትን፥ የማይሰሙትንም፥ የማይበሉትንም፥ የማያሸቱትንም፥ በሰው እጅ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን ሌሎች አማልክት ታመልካላችሁ።