Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 26:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እነርሱ ሞተዋል፥ በሕይወት አይኖሩም፤ ጠፍተዋል፥ አይነሡም፤ ስለዚህ አንተ ጎብኝተሃቸዋል፤ አጥፍተሃቸውማል፤ መታሰቢያቸውንም ሁሉ እንዳልነበር አድርገሃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እነርሱ ሞተዋል፤ ከእንግዲህ በሕይወት አይኖሩም፤ መንፈሳቸው ተነሥቶ አይመጣም። አንተ ቀጣሃቸው፤ አጠፋሃቸው፤ መታሰቢያቸውንም ሁሉ ደመሰስህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እነዚያ ሁሉ ሞተዋል፤ ዳግመኛም በሕይወት አይኖሩም፤ አንተም ቀጥተሃቸው ስለ ተደመሰሱ፥ ዳግመኛ አይነሡም፤ መታሰቢያቸውም ጠፍቶአል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ነገር ግን ሙታን ሕይ​ወ​ትን አያ​ዩ​አ​ትም፤ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶ​ችም አያ​ስ​ነ​ሡም፤ ስለ​ዚ​ህም አንተ አም​ጥ​ተ​ሃ​ቸ​ዋል፤ አጥ​ፍ​ተ​ሃ​ቸ​ው​ማል፤ ወን​ዶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አስ​ወ​ግ​ደ​ሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እነርሱ ሞተዋል፥ በሕይወት አይኖሩም፥ ጠፍተዋል፥ አይነሡም፥ ስለዚህ አንተ ጎብኝተሃቸዋል አጥፍተሃቸውማል፥ መታሰቢያቸውንም ሁሉ ምን ምን አድርገሃል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 26:14
25 Referencias Cruzadas  

የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፥ የክፉ ስም ግን ይጠፋል።


ሰዎች፤ የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፤ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ?


ከባዓል ፔዖርም ጋር ተጣበቁ፥ የሙታንንም መሥዋዕት በሉ፥


የቀሩቱ ሙታን ግን ይህ ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ እንደገና በሕይወት አልኖሩም። ይህ የመጀመሪያው ትንሣኤ ነው።


እንዲህም አለው፦ “ተነሣ፤የሕፃኑን ነፍስ የሚፈልጉት ሞተዋልና ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ምድር ሂድ።”


በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?


ተተኪ አይኑረው፥ በቀጣይ ትውልድ ስማቸው ይደምሰስ።


አሕዛብን ገሠጽህ፥ ክፉዎችንም አጠፋህ፥ ስማቸውንም ለዘለዓለም ደመሰስህ።


በዚያም ማየትም ሆነ መስማት፥ መብላት ሆነ ማሽተት የማይችሉትን፥ በሰው እጅ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት ታመልካላችሁ።


ጌታም በዚያን ቀን እስራኤልን ከግብፃውያን እጅ አዳነ፤ እስራኤልም የግብፃውያንን ሞት በባሕር ዳር አዩ።


ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፥ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፥ ጠልህ የብርሃን ጠል ነውና፥ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።


የትዕቢት እግር አይምጣብኝ፥ የዐመጸኞችም እጅ አያስተኝ።


ያለ በደል ሮጥሁ ተዘጋጀሁም፥ ተነሥ፥ ተቀበለኝ፥ እይም።


ጆሮ አላቸው፥ አይሰሙምም፥ እስትንፋስም በአፋቸው የለም።


ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፥ ሙታን ግን አንዳችም ነገር አያውቁም፥ መታሰቢያቸውም ተረስቶአልና ከዚያ በኋላ ዋጋ የላቸውም።


ድንገትም ፈጥኖ የሠራዊት ጌታ በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅም ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።


አማልክቶቻቸውንም በእሳት ላይ ጥለዋል፤ የእንጨትና የድንጋይ፥ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።


ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ፥ እንዲሁ ወደ ሲኦል የሚወርድ ዳግመኛ አይወጣም።


መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፥ በሜዳም ስም አይቀርለትም።


ማኅፀን ትረሳዋለች፥ ትልም በደስታ ይጠባዋል፥ ዳግመኛም የሚያስታውሰው የለም፥ ክፋትም እንደ ዛፍ ይሰበራል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios