እግዚአብሔርም የሕፃኑን ጩኸት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን እንዲህ ሲል ጠራት፥ “አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግዚአብሔር የልጅሽን ድምፅ ባለበት ስፍራ ሰምቶአልና አትፍሪ።
ኢሳይያስ 22:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ጽዮን ሸለቆ የተነገረ ቃል። እናንተ ሁላችሁ፥ ዛሬ ወደ ሰገነት በከንቱ መውጣታችሁ ምን ሆናችኋል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ንግር፤ እስኪ ምን ቢጨንቃችሁ ነው ሁላችሁም ሰገነት ላይ የወጣችሁት? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ራእይ። እናንተ ሁላችሁ ወደ ሰገነት መውጣታችሁ ምን ማለት ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የራእይ ሸለቆ” ተብሎ ስለሚጠራው ቦታ የተነገረ ቃል ይህ ነው፤ በየቤታችሁ ሰገነት ላይ ሆናችሁ በዓል የምታከብሩት በምን ምክንያት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ሸክም። እናንተ ሁላችሁ ወደ ሰገነት መውጣታችሁ ምን ሆናችኋል? |
እግዚአብሔርም የሕፃኑን ጩኸት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን እንዲህ ሲል ጠራት፥ “አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግዚአብሔር የልጅሽን ድምፅ ባለበት ስፍራ ሰምቶአልና አትፍሪ።
ንጉሡም፥ “ምን ሆነሻል?” አላት፤ እርስዋም፥ “ይህች ሴት፦ ዛሬ እንድንበላው ልጅሽን አምጪ፤ ነገም ልጄን እንበላለን አለችኝ።
በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን ሞላ፥ አንደበታችንም ሐሤትን አደረገ፤ በዚያን ጊዜ አሕዛብ፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው” አሉ።
በየመንገድዋ ማቅ ታጠቁ፤ በየሰገነቶችዋም አልቅሱ፤ በየአደባባዮችዋም እንባን እጅግ እያፈሰሳችሁ ወዮ በሉ።
ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሁከትና የጥፋት፥ የመረገጥና የስብራትም ቀን በጽዮን ሸለቆ ውስጥ ሆኖአል። ታናሹና ታላቁም ሸሽተው በተራራ ላይ ይቅበዘበዛሉ።
የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች እንደ ቶፌት የረከሱ ይሆናሉ፤ እነዚያም በሰገነታቸው ላይ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ ያጠኑባቸው፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ ይፈርሳሉ።”
እነሆ በሜዳ ላይ ባለው ድንጋያማ ሸለቆ የምትቀመጥ ሆይ! እኔ በአንተ ላይ ነኝ፤ እናንተም፦ የሚያስደነግጠን ወይም ወደ መኖሪያችን የሚገባ ማን ነው? የምትሉ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፤
ይችን ከተማ የሚወጉ ከለዳውያን ይመጣሉ፤ ከተማዋንም በእሳት ያነድዱአታል፤ ያስቈጡኝም ዘንድ በሰገነታቸው ላይ ለበዓል ያጠኑባቸውን፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቍርባን ያፈሰሱባቸውን ቤቶች ያቃጥሉአቸዋል።
ይህም እኔን ያስቈጡኝ ዘንድ፥ እነርሱና ነገሥታቶቻቸው፥ አለቆቻቸውም፥ ካህናቶቻቸውም፥ ነቢያቶቻቸውም፥ የይሁዳም ሰዎች፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ ስለ አደረጉት ስለ እስራኤል ልጆችና ስለ ይሁዳ ልጆች ክፋት ሁሉ ነው።
ሞአብንም ለምንም እንደማይጠቅም ዕቃ ሰብሬአለሁና በሞአብ ሰገነት ሁሉ ላይ፥ በአደባባዩም ላይ ልቅሶ አለ፥” ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህ ሌሊት ይሆንባችኋል እንጂ ራእይ አይሆንላችሁም፥ ጨለማም ይሆንባችኋል እንጂ አታምዋርቱም፥ ፀሐይም በነቢያት ላይ ትገባለች፥ ቀኑም ይጠቁርባቸዋል።
እነሆም፥ ሳኦል ከእርሻው አርፍዶ መጣ፤ ሳኦልም፥ “ሕዝቡ የሚያለቅስ ምን ሆኖ ነው?” አለ። የኢያቢስንም ሰዎች ነገር ነገሩት።
ብላቴናው ሳሙኤልም በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ክቡር ነበረ፤ ራእይም አይገለጥም ነበር።