Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 18:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ወደ ዳንም ልጆች ጮኹ፤ የዳ​ንም ልጆች ፊታ​ቸ​ውን መል​ሰው ሚካን፥ “የም​ት​ጮ​ኸው ምን ሆነህ ነው?” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ከበስተኋላቸው ሆነው ሲጮኹባቸውም፣ የዳን ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው ሚካን፣ “ሰዎችህን ለውጊያ አሰባስበህ መምጣትህ ምን ሆንህና ነው?” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ከበሰተኋላቸው ሆነው ሲጮሁባቸውም፥ የዳን ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው ሚካን፥ “ሰዎችህን ለውጊያ አሰባስበህ መምጣትህ ምን ሆነህ ነው?” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ደነፋባቸው፤ ከዳን የመጡትም ሰዎች ወደ ኋላ መለስ ብለው ሚካን “ምን ሆነሃል? ይህን ሁሉ ሰውስ የሰበሰብከው ለምንድነው?” ሲሉ ጠየቁት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ወደ ዳንም ልጆች ጮኹ፥ የዳንም ልጆች ፊታቸውን መልሰው ሚካን፦ የምትጮኸው ምን ሆነህ ነው? አሉት።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 18:23
8 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕ​ፃ​ኑን ጩኸት ሰማ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከሰ​ማይ አጋ​ርን እን​ዲህ ሲል ጠራት፥ “አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የል​ጅ​ሽን ድምፅ ባለ​በት ስፍራ ሰም​ቶ​አ​ልና አት​ፍሪ።


ንጉ​ሡም፥ “ምን ሆነ​ሻል?” አላት። እር​ስ​ዋም አለች፥ “በእ​ው​ነት እኔ ባሌ የሞ​ተ​ብኝ ባል​ቴት ሴት ነኝ።


ንጉ​ሡም፥ “ምን ሆነ​ሻል?” አላት፤ እር​ስ​ዋም፥ “ይህች ሴት፦ ዛሬ እን​ድ​ን​በ​ላው ልጅ​ሽን አምጪ፤ ነገም ልጄን እን​በ​ላ​ለን አለ​ችኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ጻድቅ ነው። አም​ላ​ካ​ችን ይቅር ባይ ነው።


ስለ ጽዮን ሸለቆ የተ​ነ​ገረ ቃል። እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ ዛሬ ወደ ሰገ​ነት በከ​ንቱ መው​ጣ​ታ​ችሁ ምን ሆና​ች​ኋል?


ከሚ​ካም ቤት ሳይ​ርቁ ሚካና የሚካ ጎረ​ቤ​ቶች ጮኹ፤ የዳ​ን​ንም ልጆች ተከ​ት​ለው ደረ​ሱ​ባ​ቸው።


እር​ሱም፥ “የሠ​ራ​ኋ​ቸ​ውን አማ​ል​ክ​ቴን፥ ካህ​ኑ​ንም ይዛ​ችሁ ሄዳ​ች​ኋል፤ ለእኔ ምን ተዋ​ች​ሁ​ልኝ? እና​ን​ተስ፦ ለምን ትጮ​ኻ​ለህ እን​ዴት ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ?” አለ።


እነ​ሆም፥ ሳኦል ከእ​ር​ሻው አር​ፍዶ መጣ፤ ሳኦ​ልም፥ “ሕዝቡ የሚ​ያ​ለ​ቅስ ምን ሆኖ ነው?” አለ። የኢ​ያ​ቢ​ስ​ንም ሰዎች ነገር ነገ​ሩት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos