Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 18:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እር​ሱም፥ “የሠ​ራ​ኋ​ቸ​ውን አማ​ል​ክ​ቴን፥ ካህ​ኑ​ንም ይዛ​ችሁ ሄዳ​ች​ኋል፤ ለእኔ ምን ተዋ​ች​ሁ​ልኝ? እና​ን​ተስ፦ ለምን ትጮ​ኻ​ለህ እን​ዴት ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ?” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እርሱም፣ “እንዴት፣ ‘ምን ሆንህ’ ብላችሁ ትጠይቁኛላችሁ? የሠራኋቸውን አማልክቴንና ካህኔን ወስዳችሁ ሄዳችኋል፤ ምን የቀረኝ ነገር አለ?” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እርሱም፥ “እንዴት፥ ‘ምን ሆንክ’ ብላችሁ ትጠይቁኛላችሁ? የሠራኋቸውን አማልክቴንና ካህኔን ወስዳችሁ ሄዳችኋል፤ ምን የቀረኝ ነገር አለ?” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ሚካም “እንዴት ‘ምን ሆነሃል’ ትሉኛላችሁ? የሚያገለግለኝን ካህንና እኔ የሠራኋቸውን ጣዖቶች ዘርፋችሁ ሄዳችሁ፤ ታዲያ እኔ ምን ተረፈኝ?” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እርሱም፦ የሠራኋቸውን አማልክቴን ካህኑንም ይዛችሁ ሄዳችኋል፥ ሌላ ምን አለኝ? እናንተስ፦ ምን ሆነሃል እንዴት ትሉኛላችሁ? አለ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 18:24
15 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም የአ​ባ​ት​ህን ቤት ከና​ፈ​ቅህ ሂድ፤ ነገር ግን አም​ላ​ኮ​ቼን ለምን ሰረ​ቅህ?”


ራሔ​ልም የአ​ባ​ቷን ጣዖ​ቶች ወስዳ ከግ​መል ኮርቻ በታች ሸሸ​ገች፤ በላ​ዩም ተቀ​መ​ጠ​ች​በት። ላባም ድን​ኳ​ኑን ሁሉ ፈለገ፤ አን​ዳ​ችም አላ​ገ​ኘም።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በን​ጉሡ በአ​ሜ​ስ​ያስ ላይ መጣ፤ እን​ዲ​ህም ሲል ነቢ​ይን ላከ​በት፥ “ሕዝ​ባ​ቸ​ውን ከአ​ንተ እጅ ያላ​ዳ​ኑ​ትን የአ​ሕ​ዛ​ብን አማ​ል​ክት ስለ​ምን ፈለ​ግ​ሃ​ቸው?”


ለአ​ንተ የም​ስ​ጋና መሥ​ዋ​ዕ​ትን እሠ​ዋ​ለሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም እጠ​ራ​ለሁ።


እር​ስዋ የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎች ምድር ናትና፥ እነ​ር​ሱም በደ​ሴ​ቶ​ችዋ ይመ​ካ​ሉና ሰይፍ በው​ኆ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ር​ቃሉ።


ሰው ሁሉ ዕው​ቀ​ትን አጥ​ቶ​አል፥ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ሐሰ​ተ​ኞች ጣዖ​ታ​ትን ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የላ​ቸ​ው​ምና።


“ሐላም አመ​ነ​ዘ​ረ​ች​ብኝ፤ ወዳ​ጆ​ች​ዋ​ንም የሚ​ቀ​ር​ቡ​አ​ትን አሦ​ራ​ው​ያ​ንን በፍ​ቅር ተከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው።


አሁን ግን እን​ደ​ም​ታ​ዩ​ትና እን​ደ​ም​ት​ሰ​ሙት ይህ ጳው​ሎስ ኤፌ​ሶ​ንን ብቻ ሳይ​ሆን መላ​ውን እስ​ያን አሳተ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም መለሰ፤ በሰው እጅ የሚ​ሠ​ሩ​ት​ንም ሁሉ አማ​ል​ክት አይ​ደ​ሉም አላ​ቸው።


የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ፤” ብሎ ተናገረኝ።


ሚካም፥ “ሌዋዊ ካህን ስለ ሆነ​ልኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካም እን​ዲ​ሠ​ራ​ልኝ አሁን አው​ቃ​ለሁ” አለ።


ሰው​ዬ​ውም ሚካ የአ​ማ​ል​ክት ቤት ነበ​ረው፤ ኤፉ​ድና ተራ​ፊም አደ​ረገ፤ ከል​ጆ​ቹም አን​ዱን ቀደ​ሰው፤ ካህ​ንም ሆነ​ለት።


ወደ ዳንም ልጆች ጮኹ፤ የዳ​ንም ልጆች ፊታ​ቸ​ውን መል​ሰው ሚካን፥ “የም​ት​ጮ​ኸው ምን ሆነህ ነው?” አሉት።


የዳ​ንም ልጆች እን​ዲህ አሉት፥ “የተ​ቈጡ ሰዎች እን​ዳ​ያ​ገ​ኙ​ህና ነፍ​ስ​ህም፥ የቤተ ሰቦ​ች​ህም ነፍስ እን​ዳ​ይ​ጠ​ፋ​ብህ፥ ድም​ፅህ በእኛ መካ​ከል አይ​ሰማ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos