Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ብላ​ቴ​ናው ሳሙ​ኤ​ልም በዔሊ ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግል ነበር፤ በዚ​ያም ዘመን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ክቡር ነበረ፤ ራእ​ይም አይ​ገ​ለ​ጥም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፤ ራእይም አይታይም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ ጌታን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የጌታ ቃል ዘወትር የሚሰማ አልነበረም፤ ራእይም አይታይም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ወጣቱ ሳሙኤል በዔሊ የአመራር ሥልጣን ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ዘወትር አይሰማም ነበር፤ ራእይም አይታይም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ብላቴናውም ሳሙኤል በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፥ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፥ ራእይም አይገለጥም ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 3:1
11 Referencias Cruzadas  

እኔ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ ይለ​ኛል፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እዘ​ም​ራ​ለሁ፥


የተ​ረ​ፉ​ትም ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከ​በሩ ይሆ​ናሉ፤ ሰውም ከሰ​ን​ፔር ዕንቍ ይልቅ የከ​በረ ይሆ​ናል።


ድን​ጋጤ በድ​ን​ጋጤ ላይ ይመ​ጣል፤ ወዮታ በወ​ዮታ ላይ ይከ​ተ​ላል፤ ከነ​ቢ​ዩም ዘንድ ራእ​ይን ይሻሉ፤ ከካ​ህ​ኑም ዘንድ ሕግ፥ ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ዘንድ ምክር ይጠ​ፋል።


በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተዉት። እነ​ር​ሱም ወደ አር​ማ​ቴም ወደ ቤታ​ቸው ገቡ፤ ልጁም በካ​ህኑ በዔሊ ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግል ነበር።


ሳሙ​ኤል ግን ገና ብላ​ቴና ሳለ የበ​ፍታ ኤፉድ ታጥቆ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያገ​ለ​ግል ነበር።


የታ​መነ ካህን ለእኔ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ በል​ቤም፥ በነ​ፍ​ሴም እን​ዳለ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል፤ እኔም የታ​መነ ቤት እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ፤ ዘመ​ኑን ሁሉ እኔ በቀ​ባ​ሁት ሰው ፊት ይሄ​ዳል።


ከቤ​ት​ህም የቀ​ረው ሁሉ ይመ​ጣል፤ ከካ​ህ​ና​ትም ወደ አን​ዲቱ ዕጣ፥ እን​ጀራ ወደ​ም​በ​ላ​በት እባ​ክህ ላከኝ ብሎ ለአ​ንድ ብር መሐ​ልቅ ለቍ​ራሽ እን​ጀራ በፊቱ ይሰ​ግ​ዳል።”


ሳሙ​ኤ​ልም እስ​ኪ​ነጋ ተኛ፥ ማል​ዶም ተነ​ሥቶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ደጅ ከፈተ። ሳሙ​ኤ​ልም ራእ​ዩን ለዔሊ መን​ገር ፈራ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ በሴሎ ተገ​ለጠ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሳ​ሙ​ኤል ይገ​ለ​ጥ​ለት ነበ​ርና። ሳሙ​ኤ​ልም ከም​ድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ እንደ ሆነ ታመነ። ዔሊም እጅግ አረጀ፥ ልጆቹ ግን በክ​ፋት ጸን​ተው ኖሩ፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos