ግብፃውያንንም በጨካኝ ጌቶች እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ጨካኞች ነገሥታትም ይገዟቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ኢሳይያስ 20:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አለ፥ “ባሪያዬ ኢሳይያስ ሦስት ዓመት ራቁቱን በባዶ እግሩ እንደ ሄደ፥ እንዲሁ በግብፅና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ምልክትና ተአምራት ይደረጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ባሪያዬ ኢሳይያስ ሦስት ዓመት በግብጽና በኢትዮጵያ ለምልክትና ለማስጠንቀቂያ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንዲህ አለ፦ “አገልጋዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት እንዲሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አገልጋዬ ኢሳይያስ ዕራቊቱን በባዶ እግሩ ሦስት ዓመት ሙሉ ሲመላለስ ነበር፤ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ የሚደርስባቸውም ምልክት ይኸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም አለ፦ ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፥ |
ግብፃውያንንም በጨካኝ ጌቶች እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ጨካኞች ነገሥታትም ይገዟቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እርሱም፥ “የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊዋጋህ መጥቶአል” የሚል ወሬ ሰማ። በሰማም ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፤ እንዲህ ሲል፦
እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኀኒትህ ነኝ፤ ግብፅንና ኢትዮጵያን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ሴዎንንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።
እነሆ፥ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ለእስራኤል በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን።
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፦ ሂድ፥ ከተልባ እግር የተሠራችን መታጠቂያ ለአንተ ግዛ፤ ወገብህንም ታጠቅባት፤ በውኃውም ውስጥ አትንከራት።
ለእስራኤልም ቤት ምልክት አድርጌሃለሁና በፊታቸው ዕቃህን በትከሻህ ላይ አንግተው፤ በጨለማም ተሸክመህ ውጣ፤ ምድሪቱንም እንዳታይ ፊትህን ሸፍን።”
ሰይፍ በግብፅ ላይ ይመጣል፤ ሁከትም በኢትዮጵያ ይሆናል፤ የተገደሉትም በግብፅ ውስጥ ይወድቃሉ፤ ብዛቷንም ይወስዳሉ፤ መሠረቷም ይፈርሳል።
“እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ግብፅን የሚደግፉ ይወድቃሉ፤ የኀይልዋም ትዕቢት ይወርዳል፤ ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሰዌኔ ድረስ በእርስዋ ውስጥ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
የብረት ምጣድም ወስደህ በአንተና በከተማዪቱ መካከል ለብረት ቅጥር አድርገው፤ ፊትህንም ወደ እርስዋ አቅና፤ የተከበበችም ትሆናለች፤ አንተም ትከብባታለህ። ይህም ለእስራኤል ልጆች ምልክት ይሆናል።
ታላቁ ካህን ኢያሱ ሆይ፥ ስማ፣ በፊትህም የሚቀመጡት ባልንጀሮች ለምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፣ እነሆ፥ እኔ ባሪያዬን ቍጥቋጥ አወጣለሁ።
ምድሪቱን እንደ ሰለሉባቸው እንደ እነዚያ አርባ ቀኖች ቍጥር ስለ ኀጢአታችሁ ሁሉ አርባው ቀን አርባ ዓመት፥ አንዱ ቀንም አንድ ዓመት ይሁንባችሁ፤ እንግዲህ የቍጣዬን መቅሠፍት ታውቃላችሁ።