Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 13:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛል፦ ሂድ፥ ከተ​ልባ እግር የተ​ሠ​ራ​ችን መታ​ጠ​ቂያ ለአ​ንተ ግዛ፤ ወገ​ብ​ህ​ንም ታጠ​ቅ​ባት፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አት​ን​ከ​ራት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር፣ “ሄደህ ከተልባ እግር የተሠራ መቀነት ግዛ፤ ወገብህንም ታጠቅበት፤ ነገር ግን ውሃ አታስነካው” አለኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታ እንዲህ ይለኛል፦ “ሂድ፥ ከተልባ እግር የተሠራን መታጠቂያ ለእራስህ ግዛ፥ ወገብህንም ታጠቀው፤ በውኃም ውስጥ አትንከረው።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ከበፍታ የተሠራ መታጠቂያ ገዝተህ ታጠቀው፤ ውሃ ግን አታስነካው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፦ ሂድ፥ ከተልባ እግር የተሠራችን መታጠቂያ ለአንተ ግዛ፥ ወገብህንም ታጠቅባት፥ በውኃውም ውስጥ አትንከራት።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 13:1
9 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ባሪ​ያዬ ኢሳ​ይ​ያስ ሦስት ዓመት ራቁ​ቱን በባዶ እግሩ እንደ ሄደ፥ እን​ዲሁ በግ​ብ​ፅና በኢ​ት​ዮ​ጵያ ላይ ሦስት ዓመት ምል​ክ​ትና ተአ​ም​ራት ይደ​ረ​ጋል።


መታ​ጠ​ቂያ በሰው ወገብ ላይ እን​ደ​ም​ት​ጣ​በቅ፥ እን​ዲሁ ለስም፥ ለመ​መ​ኪ​ያና ለክ​ብር ሕዝብ ይሆ​ኑ​ልኝ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ሁሉ፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣ​ብ​ቄ​አ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን አል​ሰ​ሙም።”


“ተነ​ሥ​ተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፤ በዚ​ያም ቃሌን አሰ​ማ​ሃ​ለሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሂድ፤ የሸ​ክላ ሠሪ የሠ​ራ​ውን ገምቦ ግዛ፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ከካ​ህ​ናት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰን​ሰ​ለ​ትና ቀን​በር ሥራ፤ በአ​ን​ገ​ት​ህም ላይ አድ​ርግ፤


“ታላ​ላ​ቆ​ችን ድን​ጋ​ዮች በእ​ጅህ ውሰድ፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች እያዩ በጣ​ፍ​ናስ ባለው በፈ​ር​ዖን ቤት ደጅ መግ​ቢያ ሸሽ​ጋ​ቸው።


ወደ እኛም መጣና የጳ​ው​ሎ​ስን መታ​ጠ​ቂያ አን​ሥቶ እጁ​ንና እግ​ሩን በገዛ እጁ አስሮ እን​ዲህ አለ፥ “መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ ይላል፤ የዚ​ህን መታ​ጠ​ቂያ ጌታ አይ​ሁድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲህ ያስ​ሩ​ታል፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል።”


ከጥ​ንት ጀምሮ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብዙ ዐይ​ነ​ትና በብዙ ጎዳና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በነ​ቢ​ያት ተና​ገረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos