ኤልዛቤልም የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውኃ ይመግባቸው ነበር።
ኢሳይያስ 16:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርኖንም በምትኖርበት ምሽግ መጠለያን ትሠራ ዘንድ ብዙ ትመክራለች፤ በቀትር ጊዜ እንደ ሌሊት ደንግጠው ይሸሻሉ፤ ወደ እናንተም አታስገቡአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምክር ለግሱን፤ ውሳኔ ስጡን፤ በቀትር ጥላችሁን እንደ ሌሊት አጥሉብን፤ የሸሹትን ደብቁ፤ ስደተኞችን አሳልፋችሁ አትስጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክርን ለግሺ፥ ፍትህን አስፍኚ፥ በቀትር ጊዜ ጥላሽን እንደ ሌሊት አጢይ፤ ስደተኞችን ሸሽጊ፥ የሸሹትን አሳልፈሽ አትስጪ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞአብ መልእክተኞች ለይሁዳ ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “ምን ማድረግ እንደሚገባን ምከሩን፤ በቀትር ጊዜ የእናንተ ጥላ እንደ ሌሊት ጨለማ ይከልለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምክርን ምከሪ፥ ፍርድን አድርጊ፥ በቀትር ጊዜ ጥላሽን እንደ ሌሊት አድርጊ፥ የተሰደዱትን ሸሽጊ፥ የሸሹትን አትግለጪ። |
ኤልዛቤልም የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውኃ ይመግባቸው ነበር።
ለተዋረዱ ሰዎች ከተሞች ረዳት ሆነሃልና፥ በችግራቸው የተጨነቁትን በደስታ ጋረድሃቸው፤ ከክፉዎች ሰዎችም አዳንሃቸው፤ ለተጠሙት ጥላ ሆንሃቸው፤ ለተገፉትም ሕይወት ሆንሃቸው።
ሰውም ቃሉን ይሰውራል፤ በውኃ እንደሚጠልቅም ይሰወራል፤ ክብሩም በደረቅ ምድር እንደሚፈስስ ውኃ በጽዮን ይገለጣል።
ከእስራኤል የተበተኑትን የሚሰበስብ ጌታ እግዚአብሔር፦ ወደ ተሰበሰቡት ሌሎችን እሰበስብለታለሁ” ይላል።
ለተራበውም እንጀራህን አጥግበው፤ ድሆችን ወደ ቤትህ አስገብተህ አሳድራቸው፤ የተራቈተውንም ብታይ አልብሰው፤ ከሥጋ ዘመድህ አትሸሽግ።
ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፤
የዳዊት ቤት ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይነድድና ማንም ሳያጠፋው እንዳያቃጥል፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ፤ የተነጠቀውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ፤ የተነጠቀውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ፤ መጻተኛውንና ድሃአደጉን፥ ባልቴቲቱንም አትበድሉ፤ አታምፁባቸውም፤ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፣ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፣ መበለቲቱንና ደሀ አደጉን፥
ዶግም ዛፎቹን፦ በእውነት እኔን በእናንተ ላይ ካነገሣችሁኝ እሳት ከዶግ ወጥቶ የሊባኖስን ዝግባ ካልበላው ከጥላዬ በታች ታርፉ ዘንድ ኑ አለቻቸው።