Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 9:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዶግም ዛፎ​ቹን፦ በእ​ው​ነት እኔን በእ​ና​ንተ ላይ ካነ​ገ​ሣ​ች​ሁኝ እሳት ከዶግ ወጥቶ የሊ​ባ​ኖ​ስን ዝግባ ካል​በ​ላው ከጥ​ላዬ በታች ታርፉ ዘንድ ኑ አለ​ቻ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “የእሾኽ ቍጥቋጦውም ዛፎቹን፣ ‘በርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾኽ ቍጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ!’ አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የእሾኽ ቊጥቋጦውም ዛፎቹን፥ “በእርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾ ቊጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የእሾኽ ቊጥቋጦም ‘በእርግጥ ንጉሥ ልታደርጉኝ ከፈለጋችሁ፥ ኑና በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ከእሾኻማዎቹ ቅርንጫፎቼ እሳት ወጥቶ የሊባኖስ ዛፍን ያቃጥላል’ ሲል መለሰላቸው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እሾሁም ዛፎችን፦ በእውነት እኔን በእናንተ ላይ ታነግሡኝ እንደ ሆነ ኑ ከጥላዬ በታች ተጠጉ። እንዲሁም ባይሆን እሳት ከእሾህ ይውጣ፥ የሊባኖስንም ዝግባ ያቃጥል አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 9:15
19 Referencias Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ፥ “የሊ​ባ​ኖስ ኵር​ን​ችት፦ ልጅ​ህን ለልጄ ሚስት አድ​ር​ገህ ስጠው ብሎ ወደ ሊባ​ኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊ​ባ​ኖ​ስም አውሬ አልፎ ኵር​ን​ች​ቱን ረገጠ።


በም​ድር ላይ ራብን አመጣ፥ የእ​ህ​ልን ኀይል ሁሉ አጠፋ።


መቅ​ሠ​ፍቱ ከቍ​ጣው ነውና፥ መዳ​ንም ከፈ​ቃዱ ነውና፤ ማታ ልቅሶ ይሰ​ማል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆ​ናል።


ኀይ​ላ​ቸ​ውም እንደ መቃ መስዬ፥ ሥራ​ቸ​ውም እንደ ጠለ​ሸት ይሆ​ናል፤ ኃጥ​አ​ንና ዐማ​ፅ​ያ​ንም አብ​ረው ይቃ​ጠ​ላሉ፤ እሳ​ቱ​ንም የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ላ​ቸው ያጣሉ።”


ደግ​ሞም በረ​ጅሙ ከፍ ባለ​ውም በሊ​ባ​ኖስ ዝግባ ሁሉ ላይ፥ በባ​ሳ​ንም ዛፍ ሁሉ ላይ፥


እኔን ሳይ​ጠ​ይቁ በፈ​ር​ዖን ኀይል ይረዱ ዘንድ በግ​ብ​ፅም ይጠ​በቁ ዘንድ ወደ ግብፅ ይሄ​ዳሉ።


አን​ተም በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችህ በኩል እን​ዲህ ብለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተገ​ዳ​ደ​ር​ኸው፦ በሰ​ረ​ገ​ላዬ ብዛት ወደ ተራ​ሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባ​ኖስ ራስ ወጥ​ቻ​ለሁ፤ ረዣ​ዥ​ሞ​ቹ​ንም ዝግ​ባ​ዎች፥ የተ​መ​ረ​ጡ​ት​ንም ጥዶች እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ ወደ ከፍ​ታ​ውም ዳርቻ ወደ ዱሩ እገ​ባ​ለሁ፤


ሬስ። ስለ እርሱ፥ “በአ​ሕ​ዛብ ውስጥ በጥ​ላው በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን” ያል​ነው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀባ፥ የሕ​ይ​ወ​ታ​ችን እስ​ት​ን​ፋስ፥ በወ​ጥ​መ​ዳ​ቸው ተያዘ።


ከተ​መ​ረ​ጡት ጫፎ​ች​ዋም በትር እሳት ወጣች፤ ፍሬ​ዋ​ንም በላች፤ የነ​ገ​ሥ​ታ​ትም በትር ይሆን ዘንድ የበ​ረታ በትር የለ​ባ​ትም።” ይህ ሙሾ ነው፤ ለል​ቅ​ሶም ይሆ​ናል።


እነሆ አሦር ጫፉ እንደ ተዋበ፥ ችፍ​ግ​ነቱ ጥላ እንደ ሰጠ፥ ቁመ​ቱም እንደ ረዘመ፥ ራሱም ወደ ደመ​ና​ዎች እንደ ደረሰ እንደ ሊባ​ኖስ ዝግባ ነበረ።


ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም ይዘ​ረ​ጋሉ፤ ውበ​ቱም እንደ ወይራ፥ ሽታ​ውም እንደ ሊባ​ኖስ ይሆ​ናል።


እሳት ከሐ​ሴ​ቦን፥ ነበ​ል​ባ​ልም ከሴ​ዎን ከተማ ወጣ፤ እስከ ሞዓብ ድረስ በላ፤ የአ​ር​ኖን ሐው​ል​ቶ​ች​ንም ዋጠ፤


እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፤ በአደገች ጊዜ ግን፥ ከአታክልቶች ትበልጣለች የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።”


ዛፎ​ችም ዶግን፦ መጥ​ተሽ በላ​ያ​ችን ንገሺ አሉ​አት፤


አሁን እን​ግ​ዲህ አቤ​ሜ​ሌ​ክን በማ​ን​ገ​ሣ​ችሁ እው​ነ​ት​ንና ቅን​ነ​ትን አድ​ር​ጋ​ችሁ እንደ ሆነ፥ ለይ​ሩ​በ​ኣ​ልም፥ ለቤ​ቱም በጎ አድ​ር​ጋ​ችሁ እን​ደ​ሆ​ነና እንደ እጁም ዋጋ መጠን ለእ​ርሱ የተ​ገ​ባ​ውን አድ​ር​ጋ​ችሁ እንደ ሆነ፥


እን​ዲህ ባይ​ሆን ግን ከአ​ቤ​ሜ​ሌክ እሳት ትውጣ፤ የሰ​ቂ​ማ​ንም ሰዎች፥ የመ​ሐ​ሎ​ን​ንም ቤት ትብላ፤ ያም ባይ​ሆን ከሰ​ቂማ ሰዎች ከመ​ሐ​ሎ​ንም ቤት እሳት ትውጣ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ትብ​ላው።”


አቤ​ሜ​ሌ​ክም ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት ሠራ​ዊት በከ​ተ​ማ​ዪቱ መግ​ቢያ በር ሸም​ቀው ቆሙ። እነ​ዚያ ሁለቱ ሠራ​ዊት ግን ወደ ጫካው ተበ​ት​ነው አጠ​ፉ​አ​ቸው።


ሕዝ​ቡም ሁሉ እን​ዲሁ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው የዛ​ፉን ቅር​ን​ጫ​ፎች ቈረጡ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ተከ​ት​ለው በም​ሽጉ ዙሪያ አኖ​ሩ​አ​ቸው፤ ምሽ​ጉ​ንም በላ​ያ​ቸው በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉት፤ የሰ​ቂ​ማም ግንብ ሰዎች ሁሉ ደግሞ አንድ ሺህ የሚ​ያ​ህሉ ወን​ድና ሴት ሞቱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos