ዳዊትም ሞዓባውያንን መታ፤ በምድርም ጥሎ በገመድ ሰፈራቸው፤ በሁለትም ገመድ ለሞት፥ በአንድም ገመድ ለሕይወት ሰፈራቸው፤ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት።
ኢሳይያስ 16:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ምድረ በዳ አይደለችምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምድረ በዳው ማዶ ካለችው ከሴላ፣ ለምድሪቱ ገዥ፣ ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራ የበግ ጠቦት ግብር ላኩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድረ በዳ ካለችው ከሴላ በምድር ላይ ገዢ ለሆነው ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራ የበግ ጠቦቶችን ስደዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞአብ ሕዝብ ሆይ! በጽዮን ተራራ ላይ ለሚገኘው ለሀገሪቱ መሪ ከሴላ በበረሓው በኩል ጠቦቶችን እጅ መንሻ አድርጋችሁ ላኩለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ ለሰለጠነ አለቃ የበግ ጠቦቶችን በምድረ በዳ ካለችው ከሴላ ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ስደዱ። |
ዳዊትም ሞዓባውያንን መታ፤ በምድርም ጥሎ በገመድ ሰፈራቸው፤ በሁለትም ገመድ ለሞት፥ በአንድም ገመድ ለሕይወት ሰፈራቸው፤ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት።
እርሱም በጨው ሸለቆ ከኤዶምያስ ዐሥር ሺህ ሰው ገደለ፤ ሴላንም በጦርነት ወስዶ ስምዋን እስከ ዛሬ ድረስ “ዮቅትኤል” ብሎ ጠራት።
የሞዓብም ንጉሥ ሞሳ ባለ በጎች ነበር፤ ለእስራኤልም ንጉሥ መቶ ሺህ የጠጕር አውራ በጎችንና መቶ ሺህ ጠቦቶችን ይገብርለት ነበር።
ስለዚህ በዚህ መጽሐፍ ያዘዝሁህ ትእዛዝ ይህ ነው። በዚህ ገንዘብ ወይፈኖችንና አውራ በጎችን፥ ጠቦቶችንም፥ የእህላቸውንና የመጠጣቸውን ቍርባን ተግተህ ግዛ፤ በኢየሩሳሌምም ባለው በአምላካችሁ ቤት መሠዊያ ላይ አቅርባቸው።
ምድረ በዳውና ከተሞችዋ፥ የቄዳርም ነዋሪዎችና መንደሮች ድምፃቸውን ያንሡ፤ በዋሻም የሚኖሩ እልል ይበሉ፤ በተራሮችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።
አንተም የመንጋ ግንብ ሆይ፥ የጽዮን ሴት ልጅ አምባ፥ ወደ አንተ ትመጣለች፥ የቀደመችው ግዛት፥ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ትደርሳለች።