Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 15:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የዲ​ሞ​ንም ውኃ ደም ተሞ​ል​ታ​ለች፤ በዲ​ሞን ላይ ዐረ​ባ​ው​ያ​ንን አመ​ጣ​ለ​ሁና፤ የሞ​ዓ​ብ​ንና የአ​ር​ያ​ልን ዘር፥ ከኤ​ዶ​ም​ያ​ስም የተ​ረ​ፉ​ትን ወስጄ እንደ አራ​ዊት በም​ድር ላይ እሰ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የዲሞን ወንዞች በደም ተሞልተዋል፤ በዲሞን ላይ ግን ከዚያ ነገር የበለጠ አመጣለሁ፤ ከሞዓብ በሚሸሹት፣ በምድሪቱም ላይ በሚቀሩት አንበሳ እሰድዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የዲሞንም ውኃ ደም ተሞልታለች፤ ገና በዲሞን ላይ ሥቃይን እጨምራለሁ፥ ከሞዓባውያንም በሚያመልጡ፥ ከምድርም በሚቀሩ ላይ አንበሳን እሰዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በዲቦን ከተማ የሚገኘው ወንዝ በደም የተሞላ ነው፤ ሆኖም በዲቦን ላይ እግዚአብሔር ከዚያ የባሰ ነገር ያመጣል፤ ከሞአብ ሸሽተው የሚያመልጡትንና እዚያም ከሞት የተረፉትን ሁሉ አንበሳ ልኮ ያጠፋቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የዲሞንም ውኃ ደም ተሞልታለች፥ በዲሞንም ላይ ሥቃይን እጨምራለሁ፥ ከሞዓባውያንም በሚያመልጡ፥ ከምድርም በሚቀሩ ላይ አንበሳን አመጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 15:9
11 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያም መቀ​መጥ በጀ​መሩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አይ​ፈ​ሩ​ትም ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​በ​ሶ​ችን ሰደ​ደ​ባ​ቸው፤ ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸ​ውም ነበር።


ከአ​ን​በሳ ፊት እንደ ሸሸ፥ ድብም እን​ዳ​ገ​ኘው ሰው፥ ወደ ቤትም ገብቶ እጁን በግ​ድ​ግዳ ላይ እን​ዳ​ስ​ደ​ገ​ፈና እባብ እንደ ነደ​ፈው ሰው ይሆ​ናል።


“እስ​ራ​ኤል የባ​ዘነ በግ ነው፤ አን​በ​ሶች አሳ​ደ​ዱት፤ መጀ​መ​ሪያ የአ​ሦር ንጉሥ በላው፥ በመ​ጨ​ረ​ሻም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር አጥ​ን​ቱን ቈረ​ጠ​መው።”


ሰይ​ፍን ለመ​ግ​ደል፥ ውሾ​ች​ንም ለመ​ጐ​ተት፥ የሰ​ማ​ያ​ት​ንም ወፎች፥ የም​ድ​ር​ንም አራ​ዊት ለመ​ብ​ላ​ትና ለማ​ጥ​ፋት፥ አራ​ቱን ዓይ​ነት ጥፋት አዝ​ዝ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እኔ ደግሞ አግ​ድሜ በቍጣ እሄ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እንደ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ሰባት እጥፍ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


እኔ ደግሞ አግ​ድሜ በቍጣ እሄ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ሰባት እጥፍ እበ​ቀ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


እስ​ከ​ዚ​ህም ድረስ ባት​ሰ​ሙኝ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ በቅ​ጣ​ታ​ችሁ ላይ ሰባት እጥፍ መቅ​ሠ​ፍ​ትን እጨ​ም​ራ​ለሁ።


ጩኸት የሞ​ዓ​ብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፤ ልቅ​ሶ​ዋም ወደ ኤግ​ላ​ይ​ምና ወደ ኢሊም ጕድ​ጓድ ደረሰ።


ዘራ​ቸ​ውም ከሐ​ሴ​ቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፋ፤ ሴቶ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሞ​ዓብ ላይ እሳ​ትን አነ​ደዱ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios