አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚያች ምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በዚያች ምድር ነበሩ።
ሆሴዕ 6:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውን እንደሚያደቡ ወንበዴዎች፥ እንዲሁ ካህናት በሴኬም መንገድ ላይ አድብተው ይገድላሉ፤ ዐመፅንም ያደርጋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንበዴዎች ሰውን ለማጥቃት እንደሚያደቡ፣ ካህናትም በቡድን እንዲሁ ያደርጋሉ፤ በሴኬም መንገድ ላይ ሰዎችን ይገድላሉ፤ አሳፋሪም ወንጀል ይፈጽማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰው ላይ እንደሚያደቡ ወንበዴዎች እንዲሁ ካህናት አብረው ተሰበሰቡ፥ ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ ላይ ይገድላሉ፤ በእርግጥም፥ ሴሰኝነትንም ያደርጋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንበዴዎች ሰውን ለመግደል እንደሚያደቡ የካህናቱም ቡድን እንዲሁ ያደርጋል፤ ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ እንኳ እያደቡ ሰውን ይገድላሉ፤ አሳፋሪም የሆነ ወንጀል ይፈጽማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሰውም እንደሚያደቡ ወንበዴዎች፥ እንዲሁ የካህናት ወገኖች በሴኬም መንገድ ላይ ይገድላሉ፥ ሴሰኝነትንም ያደርጋሉ። |
አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚያች ምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በዚያች ምድር ነበሩ።
በመጀመሪያውም ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም እንሄድ ዘንድ ከአኅዋ ወንዝ ተነሣን፤ የአምላካችንም እጅ በላያችን ነበረ፤ በመንገድም ከጠላትና ከሚሸምቅ ሰው እጅ አዳነን።
በመካከሏ ያሉ ነቢያት እንደ አንበሳ ያገሳሉ፤ ይነጥቃሉ፤ ፈጽመውም ይቀማሉ፤ ሰውነትንም ያጠፋሉ፤ መማለጃንም ይቀበላሉ፤ በመካከልዋም መበለቶችዋ ይበዛሉ።
በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሱ ዘንድ፥ ነፍሶችንም ያጠፉ ዘንድ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው።
በውስጥሽ ደምን ያፈስሱ ዘንድ ሌቦች ሰዎች በአንቺ ውስጥ ነበሩ፤ በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ በሉ፤ በመካከልሽም የማይገባ ነገርን አደረጉ።
ሴሰኝነትሽንም፥ ከግብፅ ምድር ያወጣሽውን ዝሙትሽንም ከአንቺ አስቀራለሁ፤ ዐይንሽንም ከእንግዲህ ወዲህ ወደ እነርሱ አታነሺም፤ ግብፅንም ከዚያ ወዲያ አታስቢም።
ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! አድምጡ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ ለሚመለከት ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።
በሐሰት አድርገዋልና፥ ሌባም ገብቶአልና፥ በውጭም ወንበዴዎች ቀምተዋልና እስራኤልን እፈውስ ዘንድ በወደድሁ ጊዜ የኤፍሬም ኀጢአትና የሰማርያ ክፋት ተገለጠ።
ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረ። የካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር።
የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ጉባኤውን ሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፥ “እነሆ፥ ይህ ሰው ብዙ ተአምራት ያደርጋል፤ ምን እናድርግ?
ይህንም በሰሙ ጊዜ በአንድነት ቃላቸውን ወደ እግዚአብሔር ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፥ “ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ የፈጠርህ አንተ እግዚአብሔር ሆይ፥