Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሆሴዕ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የሚ​ያ​ድኑ አዳ​ኞች ያጠ​ም​ዱ​ባት ዘንድ ተከ​ሏት፤ እኔ ግን መካ​ሪ​ያ​ችሁ ነኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ዐመፀኞች በግድያ በርትተዋል፤ ሁሉንም እቀጣቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ዓመፀኞችም እርድ አብዝተዋል፤ እኔ ግን እነርሱን ሁሉ እገሥጻለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ዐመፀኞች የግድያ ሥራቸውን አስፋፍተዋል፤ ስለዚህ ሁሉንም እቀጣቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ዓመፀኞችም እርድ አብዝተዋል፥ እኔ ግን እነዚያን ሁሉ እዘልፋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 5:2
18 Referencias Cruzadas  

እን​ግ​ዲህ በበ​ደል ላይ በደል እየ​ጨ​መ​ራ​ችሁ ለምን ትቀ​ሠ​ፋ​ላ​ችሁ? ራስ ሁሉ ለሕ​ማም፥ ልብም ሁሉ ለኀ​ዘን ሆኖ​አል።


ምክ​ራ​ቸ​ውን ጥልቅ አድ​ር​ገው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ሰ​ውሩ ወዮ​ላ​ቸው! ሥራ​ቸ​ው​ንም በጨ​ለማ ውስጥ አድ​ር​ገው፥ “ማን ያየ​ናል? ወይስ ማን ያው​ቀ​ናል?” ለሚሉ ወዮ​ላ​ቸው!


እነ​ር​ሱም፥ “ሕግ ከካ​ህን፥ ምክ​ርም ከጠ​ቢብ፥ ቃልም ከነ​ቢይ አይ​ጠ​ፋ​ምና ኑ፤ በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ምክ​ርን እን​ም​ከር። ኑ፤ በም​ላስ እን​ም​ታው፤ ቃሉ​ንም ሁሉ አና​ዳ​ምጥ” አሉ።


አቤቱ! ዐይ​ኖ​ችህ ለሃ​ይ​ማ​ኖት አይ​ደ​ሉ​ምን? አንተ ቀሥ​ፈ​ሃ​ቸ​ዋል፤ ነገር ግን አላ​ዘ​ኑም፤ ቀጥ​ቅ​ጠ​ሃ​ቸ​ው​ማል፤ ነገር ግን ተግ​ሣ​ጽን እንቢ አሉ፤ ፊታ​ቸ​ውን ከድ​ን​ጋይ ይልቅ አጠ​ን​ክ​ረ​ዋል፤ ይመ​ለ​ሱም ዘንድ እንቢ አሉ።


እነ​ርሱ ሁሉ እጅግ ደን​ቆ​ሮ​ዎች ናቸው፤ በጠ​ማ​ማ​ነት ይሄ​ዳሉ፤ ሁሉም እንደ ናስና ብረት የዛጉ ናቸው።


ነገር ግን ሐሰት፥ ግዳ​ይና ስር​ቆት፥ ምን​ዝ​ር​ናም ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋል፤ ደም​ንም ከደም ጋር ይቀ​ላ​ቅ​ላሉ።


ስለ​ዚህ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ድ​ኋ​ቸው፤ በአ​ፌም ቃል ገደ​ል​ኋ​ቸው፤ ፍር​ዴም እንደ ብር​ሃን ይወ​ጣል።


ሰውን እን​ደ​ሚ​ያ​ደቡ ወን​በ​ዴ​ዎች፥ እን​ዲሁ ካህ​ናት በሴ​ኬም መን​ገድ ላይ አድ​ብ​ተው ይገ​ድ​ላሉ፤ ዐመ​ፅ​ንም ያደ​ር​ጋሉ።


ክፋ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ በጌ​ል​ገላ አለ፤ በዚያ ጠል​ቻ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስለ ሠሩት ክፋት ከቤቴ አሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ አል​ወ​ድ​ዳ​ቸ​ውም፤ አለ​ቆ​ቻ​ቸው ሁሉ ዐመ​ፀ​ኞች ናቸ​ውና።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos