እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ክፉ ነገርም ቢያደርግ፥ በሰዎች በትርና በሰው ልጆች አለንጋ እገሥጸዋለሁ፤
ሆሴዕ 11:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰው ገመድ በፍቅርም እስራት ሳብኋቸው፤ ለእነርሱም ፊቱን በጥፊ እንደሚመቱት ሰው ሆንሁላቸው፤ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፤ እችለውማለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰው የርኅራኄ ገመድ፣ በፍቅርም ሰንሰለት ሳብኋቸው፤ ቀንበሩን ከጫንቃቸው ላይ አነሣሁላቸው፤ ዝቅ ብዬም መገብኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰብአዊ በሆነ የርኅራኄ ገመድ በፍቅርም እስራት ሳብኋቸው፤ ለእነርሱም ቀምበርን ከጫንቃቸው ላይ እንደሚያነሣ ሆንሁ፥ እነርሱንም ጐንበስ ብዬ መገብኳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰብአዊ ርኅራኄና በፍቅር ትስስር መራኋቸው፤ ቀንበሩን ከጫንቃቸው ላይ በማንሣት እኔ ራሴ ጐንበስ ብዬ መገብኳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰው ገመድ በፍቅርም እስራት ሳብኋቸው፥ ለእነርሱም ቀምበርን ከጫንቃቸው ላይ እንደሚያነሣ ሆንሁ፥ ድርቆሽም ጣልሁላቸው። |
እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ክፉ ነገርም ቢያደርግ፥ በሰዎች በትርና በሰው ልጆች አለንጋ እገሥጸዋለሁ፤
ሙሴም፥ “እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር ይህ ነው፦ ከግብፅ ምድር በአወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን እንጀራ ያዩ ዘንድ ከእርሱ አንድ ጎሞር ሙሉ ለልጅ ልጆቻችሁ ይጠበቅ” አለ።
ከወደ ኋላህም ሳቡህ፥ በሽቱህ መዓዛም እንሮጣለን፤ ንጉሡ ወደ እልፍኙ አገባኝ፤ በአንቺ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትም እናደርጋለን፤ ከወይን ጠጅ ይልቅ ጡቶችሽን እንወዳለን፤ አንቺንም መውደድ የተገባ ነው።
በመልእክተኛም አይደለም፤ በመልአክም አይደለም፤ እርሱ ራሱ ያድናቸዋል እንጂ። እርሱ ይወዳቸዋልና፥ ይራራላቸዋልምና እርሱ ተቤዣቸው፤ ተቀበላቸውም፤ በዘመናቸውም ሁሉ ለዘለዓለም አከበራቸው።
እርስዋም እህልንና ወይንን ዘይትንም የሰጠኋት፥ ብርንና ወርቅን ያበዛሁላት እኔ እንደ ሆንሁ አላወቀችም። እርስዋ ግን ወርቁንና ብሩን ለጣዖት አደረገች።
ባሪያዎች ከነበራችሁበት ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ፤ በግልጽም አወጣኋችሁ።
በላሙ ቅቤ፥ በበጉም ወተት፥ ከፍየል ጠቦትና ከላም፥ ከጊደሮችና ከበጎች ስብ ጋር፥ ከፍትግ ስንዴ ጋር መገባቸው፤ የዘለላውንም ደም የወይን ጠጅ አድርገው ጠጡ።