Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ልጅ ይሆ​ነ​ኛል፤ ክፉ ነገ​ርም ቢያ​ደ​ርግ፥ በሰ​ዎች በት​ርና በሰው ልጆች አለ​ንጋ እገ​ሥ​ጸ​ዋ​ለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል። በደል ቢፈጽም ግን ሰዎች በሚቀጡበት በትር እቀጣዋለሁ፤ የሰው ልጆችም በዐለንጋ እንደሚገረፉ እገርፈዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል። በደል በሚፈጽምበትም ጊዜ ሰዎች በሚቀጡበት በትር እቀጣዋለሁ፤ የሰው ልጆችም በዐለንጋ እንደሚገረፉ እገርፈዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል፤ ስሕተት በሚፈጽምበትም ጊዜ አባት ልጁን እንደሚቀጣ እቀጣዋለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፥ ክፉ ነገርም ቢያደርግ፥ ሰው በሚቀጣበት በትርና በሰው ልጆች መቀጫ እገሥጸዋለሁ፥

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 7:14
19 Referencias Cruzadas  

ከመ​ላ​እ​ክ​ትስ ከሆነ ጀምሮ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ” ዳግ​መ​ኛም፥ “እኔ አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ እር​ሱም ልጄ ይሆ​ነ​ኛል” ያለው ከቶ ለማን ነው?


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፦ ልጅ ይሆ​ነኝ ዘንድ መር​ጬ​ዋ​ለ​ሁና፥ እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለ​ሁና ልጅህ ሰሎ​ሞን ቤቴ​ንና አደ​ባ​ባ​ዮ​ቼን ይሠ​ራል።


እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ልጄ ይሆ​ነ​ኛል፤ ከአ​ንተ አስ​ቀ​ድሞ ከነ​በ​ሩት እን​ዳ​ራ​ቅሁ፥ ምሕ​ረ​ቴን ከእ​ርሱ አላ​ር​ቅም።


ሰውም ልጁን እን​ደ​ሚ​ገ​ሥጽ እን​ዲሁ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ተን እን​ዲ​ገ​ሥጽ በል​ብህ ዕወቅ።


ነገር ግን በተ​ፈ​ረ​ደ​ብን ጊዜ ከዓ​ለም ጋር እን​ዳ​ን​ኰ​ነን በጌታ እን​ገ​ሠ​ጻ​ለን።


አድ​ንህ ዘንድ ከአ​ንተ ጋር ነኝና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተ​ንም የበ​ተ​ን​ሁ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለሁ፤ አን​ተን ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ህም፤ በመ​ጠን እቀ​ጣ​ሃ​ለሁ፥” ያለ ቅጣ​ትም ከቶ አል​ተ​ው​ህም።”


እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” አለ።


“ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገ​ሥ​ጸው ሰው ብፁዕ ነው፤ ስለ​ዚህ ሁሉን የሚ​ች​ለ​ውን የአ​ም​ላ​ክን ተግ​ሣጽ አት​ናቅ።


አባት እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ አለ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል፤ አምላክም እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።


ነገር ግን እና​ን​ተና ልጆ​ቻ​ችሁ እኔን ትታ​ችሁ ወደ ኋላ ብት​መ​ለሱ ለሙሴ በፊ​ታ​ችሁ የሰ​ጠ​ሁ​ትን ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን ባት​ጠ​ብቁ፥ ሄዳ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ ብት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥


መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም ሁሉ ከእጁ አል​ወ​ስ​ድም፤ ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን ስለ ጠበ​ቀው ስለ መረ​ጥ​ሁት ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊት ግን በዕ​ድ​ሜው ሁሉ አለቃ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል፤ ልጅም ይሆ​ነ​ኛል፤ እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ የመ​ን​ግ​ሥ​ቱ​ንም ዙፋን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እና​ገር ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለኝ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔም ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios