እርሱም፥ “አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም መልካምን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና” አለ።
ሆሴዕ 11:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ኤፍሬምን ወደድሁት፤ በክንዴም ተቀበልሁት፤ እኔም እፈውሳቸው እንደ ነበርሁ አላወቁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤፍሬምን እጁን ይዤ፣ እንዲራመድ ያስተማርሁት እኔ ነበርሁ፤ ነገር ግን የፈወስኋቸው እኔ እንደ ሆንሁ፣ እነርሱ አላስተዋሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ኤፍሬምን ክንዱን ይዤ መራመድን አስተማርሁት፤ እኔም እፈውሳቸው እንደ ነበርሁ አላወቁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጆቻቸውን ይዤ በእግራቸው መረማመድን ያስተማርኳቸው እኔ ነበርኩ፤ ዕቅፍ አድርጌም ይዤአቸው ነበርኩ፤ እነርሱ ግን እኔ እንደምንከባከባቸው አላወቁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ኤፍሬምን ክንዱን ይዤ በእግሩ እንዲሄድ መራሁት፥ እኔም እፈውሳቸው እንደ ነበርሁ አላወቁም። |
እርሱም፥ “አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም መልካምን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና” አለ።
በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ እንደ ንስር ክንፍም እንደ ተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።
አምላክህንም እግዚአብሔርን ታመልካለህ፤ እኔ እህልህንና ወይንህን፥ ውኃህንም እባርካለሁ፤ በሽታንም ከአንተ አርቃለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአልና፥ “ሰማይ ስማ፤ ምድርም አድምጪ፤ ልጆችን ወለድሁ፤ አሳደግሁም፤ እነርሱም ዐመፁብኝ።
እግዚአብሔርም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ በመቅሠፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።
እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ የእስራኤልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከማኅፀንም ጀምሮ የተሸከምኋችሁ፥ ከሕፃንነትም ጀምሮ ያስተማርኋችሁ፥ ስሙኝ።
በመልእክተኛም አይደለም፤ በመልአክም አይደለም፤ እርሱ ራሱ ያድናቸዋል እንጂ። እርሱ ይወዳቸዋልና፥ ይራራላቸዋልምና እርሱ ተቤዣቸው፤ ተቀበላቸውም፤ በዘመናቸውም ሁሉ ለዘለዓለም አከበራቸው።
እኔ ከክፉ ቍስልሽ እፈውስሻለሁ፤ ጤናሽን እመልስልሻለሁ፤ ቍስልሽንም እፈውሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ማንም የማይሻት፥ የተጣለች ጽዮን ብለው ጠርተውሻልና።”
አሦር አያድነንም፤ በፈረስም ላይ አንቀመጥም፤ ድሃአደጉም በአንተ ዘንድ ይቅርታን ያገኛልና ከእንግዲህ ወዲህ የእጆቻችንን ሥራ አምላኮቻችን ናችሁ አንላቸውም።”
እርስዋም እህልንና ወይንን ዘይትንም የሰጠኋት፥ ብርንና ወርቅን ያበዛሁላት እኔ እንደ ሆንሁ አላወቀችም። እርስዋ ግን ወርቁንና ብሩን ለጣዖት አደረገች።
በሐሰት አድርገዋልና፥ ሌባም ገብቶአልና፥ በውጭም ወንበዴዎች ቀምተዋልና እስራኤልን እፈውስ ዘንድ በወደድሁ ጊዜ የኤፍሬም ኀጢአትና የሰማርያ ክፋት ተገለጠ።
ወደዚህም ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ፥ ሰው ልጁን እንዲመግብ አምላካችሁ እግዚአብሔር በምድረ በዳ እንደመገባችሁ እናንተ አይታችኋል።
አምላክህ እግዚአብሔር ይፈትንህ ዘንድ፥ በልብህም ያለውን ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያስጨንቅህ በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስብ።