ሐጌ 2:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ገና አንድ ጊዜ በቅርብ ዘመን እኔ ሰማያትንና ምድርን ባሕርንና የብስንም አናውጣለሁ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በቅርቡ፣ አንድ ጊዜ እንደ ገና ሰማያትንና ምድርን፣ ባሕሩንና የብሱን አናውጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ እንደገና በቅርብ ጊዜ ሰማያትንና ምድርን ባሕርንና የብስን አናውጣለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደገና ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንና የብስን አናውጣለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ገና አንድ ጊዜ በቅርብ ዘመን እኔ ሰማያትንና ምድርን ባሕርንና የብስንም አናውጣለሁ፥ |
የእግዚአብሔር ሕግ ንጹሕ ነው፤ ነፍስንም ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትንም ጠቢባን ያደርጋል።
ስለዚህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት በጽኑ ቍጣው ቀንም ሰማያት ይንቀጠቀጣሉ፤ ምድርም ከመሠረቷ ትናወጣለች።
እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ እግዚአብሔርን ከመፍራትና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃቃት ውስጥ ያገቡአቸዋል።
“እነሆ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የሰጠሁትን መልካም የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “የባቢሎን ንጉሥ ቤት እንደ ተረገጠ አውድማ ናት፤ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል።
ከእግዚአብሔርም ፊት የተነሣ የባሕር ዓሣዎችና የሰማይ ወፎች፥ የምድረ በዳም አራዊት፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፤ ተራሮችም ይገለባበጣሉ፤ ገዳላገደሎችም ይወድቃሉ፤ ቅጥርም ሁሉ ወደ ምድር ይወድቃል።
እግዚአብሔርም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፤ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ ይራራል፤ የእስራኤልንም ልጆች ያጸናል።
ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኵል በድናቸውን ይመለከታሉ፤ በድናቸውም ወደ መቃብር ሊገባ አይፈቅዱም።