Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ራእይ 11:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኵል በድናቸውን ይመለከታሉ፤ በድናቸውም ወደ መቃብር ሊገባ አይፈቅዱም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከወገን፣ ከነገድ፣ ከቋንቋና ከሕዝብ የመጡ ሰዎች ሬሳቸውን ሦስት ቀን ተኩል ይመለከታሉ፤ ሬሳቸውም እንዳይቀበር ይከለክላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኩል በድናቸውን ይመለከታሉ፤ በድናቸውም ወደ መቃብር እንዲገባ አይፈቅዱም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ልዩ ልዩ ወገንና፥ ነገድ፥ ልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪዎችና ሕዝቦች ሦስት ቀን ተኩል ሬሳቸውን ይመለከታሉ፤ ሬሳቸው እንዳይቀበርም ይከለክላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኵል በድናቸውን ይመለከታሉ፥ በድናቸውም ወደ መቃብር ሊገባ አይፈቅዱም።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 11:9
14 Referencias Cruzadas  

ተመ​ል​ሰ​ህም፦ እን​ጀራ አት​ብላ፥ ውኃም አት​ጠጣ ባለህ ስፍራ እን​ጀራ በል​ተ​ሃ​ልና፥ ውኃም ጠጥ​ተ​ሃ​ልና ሬሳህ ወደ አባ​ቶ​ችህ መቃ​ብር አይ​ገ​ባም።”


ሰው መቶ ልጆች ቢወ​ልድ፥ ብዙ ዘመ​ንም በሕ​ይ​ወት ቢኖር፥ ዕድ​ሜ​ውም ብዙ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መል​ካ​ምን ባት​ጠ​ግብ፥ መቃ​ብ​ር​ንም ባያ​ገኝ፥ እኔ ስለ እርሱ፥ “ከእ​ርሱ ይልቅ ጭን​ጋፍ ይሻ​ላል” አልሁ።


ለሚ​ያ​ዋ​ር​ዱ​አ​ችሁ ወዮ​ላ​ቸው! እና​ን​ተን ግን የሚ​ያ​ዋ​ር​ዳ​ችሁ የለም፤ የሚ​ወ​ነ​ጅ​ላ​ችሁ እና​ን​ተን የሚ​ወ​ነ​ጅል አይ​ደ​ለም፤ ወን​ጀ​ለ​ኞች ይጠ​መ​ዳሉ፤ ይያ​ዛ​ሉም፤ ብል እን​ደ​በ​ላው ልብ​ስም ያል​ቃሉ።


የዚህ ሕዝብ ሬሳ ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናል፥ የሚ​ቀ​ብ​ራ​ቸው የለ​ምና።


“በብዙ ወገኖችና በአሕዛብም በቋንቋዎችም በነገሥታትም ላይ እንደ ገና ትንቢት ትናገር ዘንድ ይገባሃል፤” ተባልሁ።


ከሦስቱ ቀን ተኵልም በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው፤ በእግሮቻቸውም ቆሙ፤ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው።


ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፤ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።


አለኝም “ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውሃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።


መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos