እናንተ የምቷጉ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ተሰለፉ፤ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ነገም ውጡባቸው።”
ሐጌ 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንፈሴም በመካከላችሁ ይኖራልና አትፍሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ከግብጽ በወጣችሁ ጊዜ የገባሁላችሁ ቃል ይህ ነው፤ መንፈሴም በመካከላችሁ ይሆናልና አትፍሩ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ የገባሁላችሁ ቃል ነው መንፈሴ በመካከላችሁ ይቆማልና አትፍሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ ‘እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ’ ብዬ በሰጠሁት የተስፋ ቃል መሠረት አሁንም መንፈሴ ከእናንተ ጋር ስለ ሆነ አይዞአችሁ አትፍሩ” ብሎ ነገራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንፈሴም በመካከላችሁ ይኖራልና አትፍሩ። |
እናንተ የምቷጉ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ተሰለፉ፤ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ነገም ውጡባቸው።”
ያስተምራቸውም ዘንድ መልካሙን መንፈስህን ሰጠሃቸው፤ መናህንም ከአፋቸው አልከለከልህም፤ ለጥማታቸውም ውኃን ሰጠሃቸው።
ነገር ግን ብዙ ዓመታት ታገሥሃቸው፤ በነቢያትህም እጅ በመንፈስህ መሰከርህባቸው፤ አላደመጡም፤ ስለዚህም በምድር አሕዛብ እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው።
በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ እንደ ንስር ክንፍም እንደ ተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።
ሙሴም ገባ፤ ለሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃሎች ሁሉ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፥ “እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እንሰማለን፤ እናደርጋለንም” ብለው መለሱ።
ሙሴም ደሙን ወስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው፤ በዚህ ቃል ሁሉ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ያደረገው የቃል ኪዳኑ ደም እነሆ” አለ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ እኔ በሕዝብህ ፊት ሁሉ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ በምድር ሁሉ፥ በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያልተደረገውን ታላቅ ተአምራትን አደርግልሃለሁ፤ እኔም የማደርግልህ ነገር ድንቅ ነውና አንተ በመካከሉ ያለህበት ይህ ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔርን ሥራ ያያል።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በአሕዛብ ዘንድ እርግማን እንደ ነበራችሁ፥ እንዲሁ አድናችኋለሁ፥ በረከትም ትሆናላችሁ፣ አትፍሩ፥ እጃችሁንም አበርቱ።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘ጳውሎስ ሆይ፥ አትፍራ፤ በቄሣር ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ ከአንተም ጋር የሚሄዱትን ሁሉ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለአንተ ሰጥቶሃል።’
እነሆ አዝዝሃለሁ፤ በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ በርታ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥም።”
እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “አትፍራ፤ አትደንግጥ፤ ተዋጊዎችን ሁሉ ከአንተ ጋር ውሰድ፤ ተነሥተህም ወደ ጋይ ውጣ፤ እነሆ፥ የጋይንም ንጉሥ፥ ሕዝቡንም ከተማውንም ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ።
ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ አላቸው፥ “አትፍሩ፤ በእውነት ይህን ክፋት ሁሉ አደረጋችሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ አምልኩት እንጂ እግዚአብሔርን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ።