ዕንባቆም 2:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰውን ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ አንተ ብዙዎችን አሕዛብን በዝብዘሃልና ከአሕዛብ የቀሩት ሁሉ ይበዘብዙሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ብዙ ሕዝብ ስለ ዘረፍህ፣ የተረፉት ሕዝቦች ይዘርፉሃል፤ የሰው ደም አፍስሰሃልና፤ አገሮችንና ከተሞችን፣ በውስጣቸው የሚኖሩትን ሁሉ አጥፍተሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ብዙ አሕዛብን በዝብዘሃልና፥ የሰውን ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርሷም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ ከአሕዛብ የቀሩት ሁሉ ይበዘብዙሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የብዙ ሕዝቦችን ንብረት ስለ ዘረፋችሁ ከእነርሱ የተረፉት የእናንተን ንብረት ይዘርፋሉ፤ ይህም የሚሆነው እናንተ ሰዎችን ስለ ገደላችሁ፥ ምድሪቱን ከተሞችንና በእነርሱ የሚኖሩትን ስላጠፋችሁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰውን ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ አንተ ብዙዎችን አሕዛብን በዝብዘሃልና ከአሕዛብ የቀሩት ሁሉ ይበዘብዙሃል። |
ለሚያዋርዱአችሁ ወዮላቸው! እናንተን ግን የሚያዋርዳችሁ የለም፤ የሚወነጅላችሁ እናንተን የሚወነጅል አይደለም፤ ወንጀለኞች ይጠመዳሉ፤ ይያዛሉም፤ ብል እንደበላው ልብስም ያልቃሉ።
በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሽ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ለሽማግሌዎቻቸው አልራራሽም፤ ቀንበራቸውንም እጅግ አክብደሻል።
የገዛ ራሱም ምድር ጊዜ እስኪመጣ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጁ ለልጅ ልጁም ይገዛሉ፤ በዚያን ጊዜም ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት ለእርሱ ይገዙለታል።
ስለዚህ የሚበሉህ ሁሉ ይበላሉ፤ የሚማርኩህም ሁላቸው ይማረካሉ፤ የዘረፉህም ይዘረፋሉ፤ የሚማርኩህንም ሁሉ ለመማረክ አሳልፌ እሰጣለሁ።
“እናንተ ቀስትን የምትገትሩ ሰዎች ሁሉ፥ በባቢሎን ላይ በዙሪያዋ ተሰለፉ፤ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርታለችና ወርውሩባት፤ እርስዋንም ከመውጋት ቸል አትበሉ፤
የአምላካችንን የእግዚአብሔርን በቀል፥ የመቅደሱንም በቀል፥ በጽዮን ይነግሩ ዘንድ ሸሽተው ከባቢሎን ሀገር ያመለጡት ሰዎች ድምፅ ተሰምቶአል።
ሰይፍ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ላይ፥ በመካከልዋም በተቀላቀሉ ሕዝብ ላይ አለ፤ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍ በመዝገቦችዋ ላይ አለ፤ ይበተናሉም።
በጽዮን በዐይናችሁ ፊት ስለ ሠሩት ክፋታቸው ሁሉ በባቢሎንና በከለዳውያን ምድር የሚኖሩትን ሁሉ እበቀላለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
በባቢሎንም ላይ እበቀላለሁ፤ የዋጠችውንም ከአፍዋ አስተፋታለሁ፤ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርስዋ አይሰበሰቡም፤ የባቢሎንም ቅጥሮች ይወድቃሉ።
አጥፊዎች ከሰሜን ይመጡባታልና ሰማይና ምድር፥ በእነርሱም ያለው ሁሉ ስለ ባቢሎን ደስ ይላቸዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።
በንግድህም ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ፤ ኀጢአትንም ሠራህ፤ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፤ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ! ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።
እንጨትን ከሜዳ አይወስዱም፤ ከዱርም አይቈርጡም፤ ነገር ግን የጦር መሣሪያን በእሳት ያነድዳሉ፤ የገፈፉአቸውንም ይገፍፋሉ፤ የበዘበዙአቸውንም ይበዘብዛሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“የእግዚአብሔር ቀን በአሕዛብ ሁሉ ላይ ቀርቦአልና፥ አንተ እንደ አደረግኸው እንዲሁ ይደረግብሃል፤ ፍዳህም በራስህ ላይ ይመለሳል።
የሰውንም ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ይከድንሃል፣ የአራዊትም አደጋ ያስፈራራሃል።
እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፣ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዓይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።
በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።