ኤርምያስ 30:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ስለዚህ የሚበሉህ ሁሉ ይበላሉ፤ የሚማርኩህም ሁላቸው ይማረካሉ፤ የዘረፉህም ይዘረፋሉ፤ የሚማርኩህንም ሁሉ ለመማረክ አሳልፌ እሰጣለሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 “ ‘ነገር ግን አሟጥጠው የበሉህ ሁሉ እንደዚያው ይበላሉ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ለምርኮ ዐልፈው ይሰጣሉ፤ የሚዘርፉህ ይዘረፋሉ፤ የሚበዘብዙህም ሁሉ ይበዘበዛሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ስለዚህ የሚውጡህ ሁሉ ይዋጣሉ፥ ጠላቶችህም ሁሉ አንድም ሳይቀሩ ይማረካሉ፤ የዘረፉህም ይዘረፋሉ፥ የበዘበዙህንም ሁሉ ለመበዝበዝ አሳልፌ እሰጣለሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ነገር ግን እናንተን ግጠው የበሉአችሁ ሁሉ እነርሱም በፈንታቸው ተግጠው ይበላሉ፤ ጠላቶቻችሁ ሁሉ ተማርከው ይወሰዳሉ፤ ሲዘርፉአችሁ የነበሩት ሁሉ ይዘረፋሉ። የቀሙአችሁ ሁሉ እነርሱም በተራቸው እንዲቀሙ አደርጋለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ስለዚህ የሚውጡህ ሁሉ ይዋጣሉ፥ ጠላቶችህም ሁላቸው ይማረካሉ፥ የዘረፉህም ይዘረፋሉ፥ የበዘበዙህንም ሁሉ ለመበዝበዝ አሳልፌ እሰጣለሁ። Ver Capítulo |