Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕንባቆም 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አንተ ብዙ አሕዛብን በዝብዘሃልና፥ የሰውን ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርሷም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ ከአሕዛብ የቀሩት ሁሉ ይበዘብዙሃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 አንተ ብዙ ሕዝብ ስለ ዘረፍህ፣ የተረፉት ሕዝቦች ይዘርፉሃል፤ የሰው ደም አፍስሰሃልና፤ አገሮችንና ከተሞችን፣ በውስጣቸው የሚኖሩትን ሁሉ አጥፍተሃል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የብዙ ሕዝቦችን ንብረት ስለ ዘረፋችሁ ከእነርሱ የተረፉት የእናንተን ንብረት ይዘርፋሉ፤ ይህም የሚሆነው እናንተ ሰዎችን ስለ ገደላችሁ፥ ምድሪቱን ከተሞችንና በእነርሱ የሚኖሩትን ስላጠፋችሁ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የሰውን ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ አንተ ብዙዎችን አሕዛብን በዝብዘሃልና ከአሕዛብ የቀሩት ሁሉ ይበዘብዙሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የሰውን ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ አንተ ብዙዎችን አሕዛብን በዝብዘሃልና ከአሕዛብ የቀሩት ሁሉ ይበዘብዙሃል።

Ver Capítulo Copiar




ዕንባቆም 2:8
33 Referencias Cruzadas  

አንቺ ፈራሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ስለ ተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ ነው።


ምክንያቱም ጌታ ለእነርሱ ይሟገታልና፥ የቀሙአቸውንም ሰዎች ሕይወት ይቀማልና።


አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፥ አንተም ሳትካድ ክህደትን የምትፈጽም ወዮልህ! ማጥፋትን በተውክ ጊዜ ትጠፋለህ፤ መካድን በተውክ ጊዜ ትካዳለህ።


አንበጣ እንደሚሰበሰብ ምርኮአችሁ ትሰብስባለች፤ ኩብኩባም እንደሚዘል ሰዎች ይዘልሉበታል።


በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሁ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ከእነርሱ ጋር ምሕረት አላደረግሽም፤ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል።


በራሱ ምድር ላይ መውደቅያው እስከሚመጣ ጊዜ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጁም ለልጅ ልጁም ያገለግላሉ፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እርሱን አገልጋይ ያደርጉታል።


ስለዚህ የሚውጡህ ሁሉ ይዋጣሉ፥ ጠላቶችህም ሁሉ አንድም ሳይቀሩ ይማረካሉ፤ የዘረፉህም ይዘረፋሉ፥ የበዘበዙህንም ሁሉ ለመበዝበዝ አሳልፌ እሰጣለሁ።


እናንተ ቀስትን የምትገትሩ ሰዎች ሁሉ፥ ባቢሎንን ዙሪያዋን ክበቡ፤ በጌታ ላይ ኃጢአት ሠርታለችና ወርውሩባት ፍላጻንም አታስቀሩ።


የአምላካችንን የጌታን በቀል ስለ መቅደሱም ሲል የሚበቀለውን በቀል በጽዮን ለመናገር ከባቢሎን ምድር የሚመጡትን የኰብላዮችና የስደተኞች ድምፅ አድምጡ።


ሰይፍ በፈረሶችዋና በሰረገሎችዋ ላይ በመካከልዋም ባሉት በባዕድ ሕዝብ ሁሉ ላይ አለ፥ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍም በመዝገቦችዋ ላይ አለ እነርሱም ይበዘበዛሉ።


አንቺ በብዙ ውኃ አጠገብ የተቀመጥሽ፥ በመዝገቦችም የበለጠግሽ ሆይ! የእንጀራሽ ገመድ ተበጥሶዋል ፍጻሜሽ ደርሶአል።


በጽዮን በዓይናችሁ ፊት ስለ ሠሩት ክፋታቸው ሁሉ በባቢሎንና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ፍዳቸውን እከፍላለሁ፥ ይላል ጌታ።


በባቢሎንም ውስጥ ቤልን እቀጣለሁ የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ፤ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርሱ አይነጉዱም፥ የባቢሎንም ቅጥር ወድቆአል።


አጥፊዎች ከሰሜን ይመጡባታልና ሰማይና ምድር በእነርሱም ያለው ሁሉ በባቢሎን ላይ እልል ይላሉ፥ ይላል ጌታ።


ባቢሎን በድንገት ወደቀች ተሰበረችም፤ አልቅሱላት፥ ምናልባት ትፈወስ እንደሆነ ለቁስልዋ የሚቀባውን መድኃኒት ውሰዱላት።


በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ፤ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፤ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።


በጦር መሣሪያው እሳትን ያነድዳሉ እንጂ እንጨትን ከሜዳ አይሸከሙም፥ ከዱርም አይቆርጡም፤ የዘረፉአቸውን ይዘርፋሉ የበዘበዙአቸውንም ይበዘብዛሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


“በንጉሥ ቅጥሮቻቸውም ግፍንና ቅሚያን የሚያከማቹ ቅን ነገር እንዴት እንደሚደረግ አያውቁም፥” ይላል ጌታ።


የጌታ ቀን በአሕዛብ ሁሉ ላይ ቀርቧልና፥ አንተ እንዳደረግኸው እንዲሁ ይደረግብሃል፥ ፍዳህም በራስህ ላይ ይመለሳል።


ብዙ ሕዝቦችን ቆራርጠህ ለቤትህ እፍረትን መክረሃል፥ በነፍስህም ላይ ኃጢአትን አድርገሃል።


ከሰው ደም፥ በምድሪቱ፥ በከተማይቱና በእርሷም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ከተደረገው ዓመጽ የተነሣ፤ በሊባኖስ ላይ የተደረገው ዓመጽ ይከድንሃል፤ የአራዊትም ጥፋት ያስፈራቸዋል።


እኔ ብዙም ሳልቆጣቸው እነርሱ ክፋትን ስላገዙት፥ በምቾት በሚኖሩት አሕዛብ ላይ እጅግ ተቈጥቻለሁ።


ጌታም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፤ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዐይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።


በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos