ዘፍጥረት 8:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያዉን ሠራ፥ ከንጹሕም እንስሳ ሁሉ፥ ከንጹሓን ወፎችም ሁሉ ወሰደ፤ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀረበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኖኅ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ መሠዊያው ላይ ንጹሕ ከሆኑት እንስሳት ሁሉ፣ እንዲሁም ንጹሕ ከሆኑት ወፎች የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኖኅም ለጌታ መሠውያን ሠራ፤ ንጹሕ ከሆኑት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ከየዓይነቱ አንዳንድ ወሰደ፤ መሥዋዕት እንዲሆኑም ሁሉንም በመሠዊያው ላይ አቃጠላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኖኅ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ፤ ንጹሕ ከሆኑት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ከየዐይነቱ አንዳንድ ወሰደ፤ መሥዋዕት እንዲሆኑም ሁሉንም በመሠዊያው ላይ አቃጠላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያውን ሠራ፥ ከንጽሕም እንስሳ ሁሉ ከንጹሐን ወፎችን ሁሉ ወሰደ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀርበ። |
“የምትወድደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ከፍተኛው ተራራ ሂድ፤ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው።
እግዚአብሔር ወዳለውም ወደዚያ ቦታ ደረሱ፤ አብርሃምም በዚያ መሠዊያዉን ሠራ፤ ዕንጨትንም ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያዉ በዕንጨቱ ላይ በልቡ አስተኛው።
በዚያም ለአምላኩ ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ፤ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ፤ በዚያም ድንኳን ተከለ፤ የይስሐቅም ሎሌዎች በዚያ ጕድጓድ ማሱ።
እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው፥ “ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፤ በዚያም ኑር፤ ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጥሁልህ ለእኔ መሥውያን ሥራ።”
በዚያም መሠውያዉን ሠራ፤ የዚያንም ቦታ ስም ቤቴል ብሎ ጠራው፤ እርሱ ከወንድሙ ከዔሳው ፊት በሸሸበት ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ተገልጦለት ነበርና።
አቤልም ደግሞ ከበጎቹ መጀመሪያ የተወለደውንና ከሰቡት አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤
ከንጹሕ የሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ የሰማይ ወፍም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለምግብና ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ።
የግብዣውም ቀኖች በተፈጸሙ ጊዜ ኢዮብ ይልክና ይቀድሳቸው ነበር፤ በማለዳም ገሥግሦ፦ ስለ ልጆቹ በቍጥራቸው መሥዋዕት ያቀርብ ነበር፤ አንድ ወይፈን ስለ ነፍሳቸው የኀጢአት መሥዋዕት ያቀርብ ነበር፤ ኢዮብ፥ “ምናልባት ልጆቼ በልባቸው በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ነገር ያስቡ ይሆናል” ይል ነበርና።
ሙሴም አለው፥ “አይሆንም! አንተ ደግሞ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የምንሠዋው መሥዋዕትንና የሚቃጠል መሥዋዕትን ትሰጠናለህ።
አውራንም በግ በሞላው በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ፤ ስለ ጣፋጭ ሽታ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው፤ ለእግዚአብሔር የቀረበ የእሳት ቍርባን ነው።
ከእጃቸውም ትቀበለዋለህ፤ በመሥዊያውም ላይ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር በእግዚአብሔር ፊት በጎ መዓዛ እንዲሆን ታቃጥለዋለህ፤ እርሱ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ነው።
ወንድሞቻችን፥ ሰውነታችሁን ለእግዚአብሔር ሕያውና ቅዱስ፥ ደስ የሚያሰኝም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እማልዳችኋለሁ። ይህም በዕውቀት የሚሆን አገልግሎታችሁ ነው።
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤