Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 8:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ከዚያም ኖኅ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ መሠዊያው ላይ ንጹሕ ከሆኑት እንስሳት ሁሉ፣ እንዲሁም ንጹሕ ከሆኑት ወፎች የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ኖኅም ለጌታ መሠውያን ሠራ፤ ንጹሕ ከሆኑት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ከየዓይነቱ አንዳንድ ወሰደ፤ መሥዋዕት እንዲሆኑም ሁሉንም በመሠዊያው ላይ አቃጠላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ኖኅ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ፤ ንጹሕ ከሆኑት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ከየዐይነቱ አንዳንድ ወሰደ፤ መሥዋዕት እንዲሆኑም ሁሉንም በመሠዊያው ላይ አቃጠላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ኖኅም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያ​ዉን ሠራ፥ ከን​ጹ​ሕም እን​ስሳ ሁሉ፥ ከን​ጹ​ሓን ወፎ​ችም ሁሉ ወሰደ፤ በመ​ሠ​ው​ያ​ውም ላይ መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያውን ሠራ፥ ከንጽሕም እንስሳ ሁሉ ከንጹሐን ወፎችን ሁሉ ወሰደ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀርበ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 8:20
27 Referencias Cruzadas  

እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው።


እግዚአብሔር ወደ አመለከተው ቦታ እንደ ደረሱ፣ አብርሃም መሠዊያ ሠራ፤ በላዩም ላይ ዕንጨት ረበረበ፤ ልጁን ይሥሐቅንም አስሮ በመሠዊያው ዕንጨት ላይ አጋደመው።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ የተቀደሰ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ገንዘቡ ያደረገው ሕዝብ ናችሁ።


እናንተ ደግሞ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕት ታቀርቡ ዘንድ፣ ቅዱሳን ካህናት ለመሆን እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ትሠራላችሁ።


በድንኳኒቱም የሚያገለግሉ ከዚያ ሊበሉ መብት ያላገኙበት መሠዊያ አለን።


ሙሴም እንዲህ አለው፤ “ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሥዋዕትና የሚቃጠል መሥዋዕት እንድንሠዋ ፍቀድልን፤


ያዕቆብም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ ስሙን ኤል-ቤቴል አለው፤ ምክንያቱም ከወንድሙ ሸሽቶ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር የተገለጠለት በዚህ ቦታ ነበር።


እግዚአብሔር ያዕቆብን፣ “ተነሥና ወደ ቤቴል ውጣ፤ እዚያም ተቀመጥ፤ ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድህ ጊዜ ለተገለጠልህ አምላክ በዚያ መሠዊያ ሥራ” አለው።


በዚያም መሠዊያ አቁሞ፣ ኤል ኤሎሄ እስራኤል ብሎ ጠራው።


ይሥሐቅም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ፤ ድንኳንም ተከለ፤ አገልጋዮቹም በዚያ የውሃ ጕድጓድ ቈፈሩ።


አብራምም ድንኳኑን ነቀለ፤ ሄዶም ኬብሮን በሚገኙት ትልልቅ የመምሬ ዛፎች አጠገብ ተቀመጠ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።


ለመጀመሪያ ጊዜም መሠዊያ ካቆመበት ስፍራ ደረሰ፤ በዚያም የእግዚአብሔርን ስም ጠራ።


ከንጹሕ እንስሳት ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፣ ንጹሕ ካልሆኑት እንስሳት ደግሞ ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት ውሰድ፤


አቤልም መጀመሪያ ከተወለዱት በጎቹ መካከል ስባቸውን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። እግዚአብሔር ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤


እግዚአብሔርም፣ “የምትወድደውን አንዱን ልጅህን፣ ይሥሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እኔ በማመለክትህ በአንዱ ተራራ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው።


እንስሳቱ ሁሉ፣ ወፎችም፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው ከመርከቧ ወጡ።


የግብዣው ጊዜ ካለፈ በኋላ ኢዮብ ልኮ ያስመጣቸውና፣ “ምናልባት ልጆቼ ኀጢአት ሠርተው፣ እግዚአብሔርንም በልባቸው ረግመው ይሆናል” በማለት ጧት በማለዳ ስለ እያንዳንዳቸው የሚቃጠል መሥዋዕት በማቅረብ ያነጻቸው ነበር፤ ኢዮብ ይህን ዘወትር ያደርግ ነበር።


እንዲሁም ከወፎች ወገን ሁሉ ሰባት ተባዕትና ሰባት እንስት፣ በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፉ ከአንተ ጋራ ታስገባለህ።


ከዚያም አውራ በጉን በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ጣፋጭ መዐዛና ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ነው።


ከዚያም ከእጃቸው ወስደህ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋራ ለእግዚአብሔር መልካም መዐዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ይህም ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።


ለሚቃጠል መሥዋዕት፣ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ አንድ ዓመት የሆነው የበግ ጠቦት፣


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios