እርስዋም፥ “ባሪያዬ ባላ እነሆ አለች፤ ወደ እርስዋ ግባ፤ በእኔም ጭን ላይ ትውለድ፤ የእርስዋም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁኑልኝ” አለች።
ዘፍጥረት 50:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም የኤፍሬምን ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ አየ። የምናሴ ልጅ የማኪር ልጆችም በዮሴፍ ጭን ላይ ተወለዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤፍሬምንም የልጅ ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ አየ። የምናሴ ልጅ ማኪር የወለዳቸውም ልጆች በዮሴፍ ጭን ላይ ተወለዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤፍሬምንም ልጆችና የልጅ ልጆች እስከሚያይ ድረስ ቈየ፤ ከምናሴ የተወለደውንም የማኪርንም ልጆች እንደ ልጆቹ አድርጎ ተቀበላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤፍሬምንም ልጆችና የልጅ ልጆች እስከሚያይ ድረስ ቈየ፤ ከምናሴ የተወለደውንም የማኪርንም ልጆች እንደ ልጆቹ አድርጎ ተቀበላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም የኤፍሬምን ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ አየ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጆችም በዮሴፍ ጭን ላይ ተወለዱ። |
እርስዋም፥ “ባሪያዬ ባላ እነሆ አለች፤ ወደ እርስዋ ግባ፤ በእኔም ጭን ላይ ትውለድ፤ የእርስዋም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁኑልኝ” አለች።
አባቱም እንቢ አለ፤ እንዲህ ሲል፥ “አውቃለሁ ልጄ ሆይ፥ አውቃለሁ፤ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል፤ ነገር ግን ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፤ ዘሩም ብዙ ሕዝብ ይሆናል።”
ኢዮብም ከደዌው ከዳነ በኋላ መቶ ሰባ ዓመት ኖረ፥ ኢዮብም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሁለት መቶ አርባ ነው። ልጆቹንና የልጅ ልጆቹንም እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ።
ሙሴም ለጋድ ልጆችና ለሮቤል ልጆች፥ ለዮሴፍም ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ፥ የአሞሬዎናውያንን ንጉሥ የሴዎንን መንግሥት፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን መንግሥት፥ ምድሪቱንም፥ ከተራሮችም ጋር ከተሞችን፥ በዙሪያቸውም ያሉትን የምድሪቱን ከተሞች ሰጣቸው።
የምናሴ ልጆች ነገድ ድንበር ይህ ነው፤ የዮሴፍ በኵር እርሱ ነውና። የምናሴም በኵር የገለዓድ አባት ማኪር ብርቱ ተዋጊ ስለ ነበረ ገለዓድንና ባሳንን ወረሰ።