ዘፍጥረት 47:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም ያዕቆብን አባቱን አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቆመው፤ ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብን ቤተ መንግሥት አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቀረበው፤ ያዕቆብም ፈርዖንን ከመረቀው በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም ያዕቆብን አባቱን አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቆመው፥ ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብን ወደ ፈርዖን አቀረበው፤ ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ያዕቆብን አባቱን አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቆመው ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው። |
ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ፥ አብርሃምና ይስሐቅ እንግዶች ሆነው ወደ ተቀመጡባት በአርባቅ ከተማ ወደምትገኘው ወደ መምሬ እርስዋም ኬብሮን ወደምትባለው መጣ።
ኢዮአብም በምድር ላይ በግንባሩ ወድቆ ሰገደለት፤ ንጉሡንም አመሰገነ፤ ኢዮአብም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የአገልጋይህን ነገር አድርገሃልና በዐይንህ ፊት ሞገስን እንዳገኘ አገልጋይህ ዛሬ ዐወቀ” አለ።
ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ ንጉሡም ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ንጉሡም ቤርዜሊን አቅፎ ሳመው፤ መረቀውም፤ ወደ ስፍራውም ተመለሰ።
ታይም የአድርአዛር ጠላት ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ስለ ተዋጋውና ስለ ገደለው፥ ታይ ልጁን ኢያዱራን ደኅንነቱን ይጠይቅ ዘንድ፥ ይመርቀውም ዘንድ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የብርና የወርቅ የናስም ዕቃ ይዞ መጣ፤
የንጉሡም አገልጋዮች ገብተው፦ ‘እግዚአብሔር የሰሎሞንን ስም ከስምህ ይልቅ መልካም ያድርግ፤ ዙፋኑንም ከዙፋንህ የበለጠ ያድርግ’ ብለው ጌታቸውን ንጉሡ ዳዊትን መረቁ፤” ንጉሡም በአልጋው ላይ ሆኖ ሰገደ።
በስምንተኛውም ቀን ሕዝቡን አሰናበተ፤ እነርሱም ንጉሡን መረቁ፤ እግዚአብሔርም ለባሪያው ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ሁሉ በልባቸው ደስ ብሏቸው፥ ሐሴትም አድርገው ወደ እየቤታቸው ሄዱ።
ኤልሳዕም ግያዝን፥ “ወገብህን ታጠቅ፤ በትሬንም በእጅህ ይዘህ ሂድ፤ ሰውም ብታገኝ ሰላም አትበል፤ እርሱም ሰላም ቢልህ አትመልስለት፤ በትሬንም በሕፃኑ ፊት ላይ አኑር” አለው።
ኅብስቱንም አነሣ፤ አመስገነ፤ ፈትቶም ሰጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ስለ እናንተ ቤዛ ሆኖ የሚሰጥ ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህንም ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤”
ዔሊም ሕልቃናንና ሚስቱን ባረካቸው፥ “ለእግዚአብሔር ስለ አገባኸው ስጦታ ፈንታ ከዚህች ሴት እግዚአብሔር ዘር ይስጥህ” አለው፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ገቡ።