በዐረብ በኩል በጌሤም ምድርም ትቀመጣለህ፤ ወደ እኔም ትቀርባለህ። አንተና ልጆችህ የልጆችህም ልጆች፥ በጎችህና ላሞችህ፥ የአንተ የሆነው ሁሉ፥
ዘፍጥረት 47:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም ገባ፤ ለፈርዖንም እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “አባቴና ወንድሞች በጎቻቸውም፥ ላሞቻቸውም፥ ያላቸውም ሁሉ ከከነዓን ምድር መጡ፤ እነርሱም እነሆ፥ ወደ ጌሤም ምድር ደረሱ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ፣ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው ከከነዓን አገር መጥተው በጌሤም ሰፍረዋል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውንና ፍየሎቻቸውን ከብቶቻቸውንና ሌላም ያላቸውን ነገር ሁሉ ይዘው ከከነዓን ወደዚህ መጥተዋል፤ አሁንም በጌሴም ምድር ይገኛሉ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውንና ፍየሎቻቸውን ከብቶቻቸውንና ሌላም ያላቸውን ነገር ሁሉ ይዘው ከከነዓን ወደዚህ መጥተዋል፤ አሁንም በጌሴም ምድር ይገኛሉ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ገባ ለፈርዖንም ነገረው እንዲህ ብሎ፦ አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውም ላሞቻቸውም ያላቸውም ሁሉ ከከነዓን ምድር ወጡ እነርሱም እነሆ በጌሤም ምድር ናቸው። |
በዐረብ በኩል በጌሤም ምድርም ትቀመጣለህ፤ ወደ እኔም ትቀርባለህ። አንተና ልጆችህ የልጆችህም ልጆች፥ በጎችህና ላሞችህ፥ የአንተ የሆነው ሁሉ፥
ዮሴፍም ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፥ “እኔ ሄጄ ለፈርዖን እንዲህ ብዬ እነግረዋለሁ፦ በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞችና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል፤
በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብፅ ሰዎች ርኩስ ነውና በዐረብ በኩል በጌሤም እንድትቀመጡ እኛ አገልጋዮችህ ከብላቴንነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ እኛም አባቶቻችንም እንስሳ አርቢዎች ነን” በሉት።
በዚያም ቀን የምድር ሁሉ አምላክ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ፥ በዚያ የውሻ ዝንብ እንዳይሆን ሕዝቤ የሚቀመጥባትን የጌሤምን ምድር እለያለሁ።
እነርሱን የቀደሳቸው እርሱ፥ የተቀደሱት እነርሱም ሁሉም በአንድነት ከአንዱ ናቸውና። ስለዚህም እነርሱን፥ “ወንድሞች” ማለትን አያፍርም።