መንጎቹንም ሁሉ፥ የቤቱንም ዕቃ ሁሉ፥ በሁለቱ ወንዞች መካከል ሳለ ያገኛቸውን ከብቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር ሄደ።
ዘፍጥረት 46:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ከብት ጠባቂዎች፥ መንጋ አርቢዎች ናቸው፤ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን፥ ያላቸውንም ሁሉ አመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹ ከብት የሚጠብቁ ስለ ሆኑ እረኞች ናቸው፤ ሲመጡም በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውንና ከብቶቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው መጥተዋል።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም በግ የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው፥ እንስሳ ያረቡ ነበርና፥ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ያላቸውንም ሁሉ አመጡ፥’ ብዬ እነግረዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ እንስሶችን የማርባት ችሎታ ያላቸው ከብት ጠባቂዎች ናቸው፤ በጎቻቸውንና ፍየሎቻቸውን፥ ከብቶቻቸውን ያላቸውን ንብረት ሁሉ ይዘው መጥተዋል’ ብዬ ልንገረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም በግ የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው እነርስሳ ያረቡ ነበርና በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ያላቸውንም ሁሉ አመጡ። |
መንጎቹንም ሁሉ፥ የቤቱንም ዕቃ ሁሉ፥ በሁለቱ ወንዞች መካከል ሳለ ያገኛቸውን ከብቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር ሄደ።
የያዕቆብም ትውልድ እንዲህ ነው። ዮሴፍ ዐሥራ ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ ከወንድሞቹ ጋር የአባቱን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ እርሱም ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዘለፋ ልጆች ጋር ሳለ ብላቴና ነበረ፤ ዮሴፍም የክፋታቸውን ወሬ ወደ አባታቸው ወደ እስራኤል ያመጣ ነበር።
እርስዋም “ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ” አለች። ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደችው። አቤልም በግ ጠባቂ ሆነ፤ ቃየልም ምድርን የሚያርስ ሆነ።
በዐረብ በኩል በጌሤም ምድርም ትቀመጣለህ፤ ወደ እኔም ትቀርባለህ። አንተና ልጆችህ የልጆችህም ልጆች፥ በጎችህና ላሞችህ፥ የአንተ የሆነው ሁሉ፥
ዮሴፍም ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፥ “እኔ ሄጄ ለፈርዖን እንዲህ ብዬ እነግረዋለሁ፦ በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞችና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል፤
በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብፅ ሰዎች ርኩስ ነውና በዐረብ በኩል በጌሤም እንድትቀመጡ እኛ አገልጋዮችህ ከብላቴንነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ እኛም አባቶቻችንም እንስሳ አርቢዎች ነን” በሉት።
ፈርዖንም የዮሴፍን ወንድሞች፥ “ሥራችሁ ምንድን ነው?” አላቸው። እነርሱም ፈርዖንን፥ “እኛ አገልጋዮችህ፥ አባታችንም ከብት ጠባቂዎች ነን” አሉት።
ኪራምም በእነዚያ መርከቦች ከሰሎሞን አገልጋዮች ጋር ባሕሩን መቅዘፍ የሚያውቁ መርከበኞች አገልጋዮቹን ላከ።
ሙሴም የአማቱን የምድያምን ካህን የዮቶርን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ በጎቹንም ወደ ምድረ በዳ ዳርቻ ነዳ፤ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።
ሳሙኤልም እሴይን፥ “ልጆችህ እኒህ ብቻ ናቸው?” አለው። እርሱም፥ “ታናሹ ገና ቀርቶአል፤ እነሆም፥ በጎችን ይጠብቃል” አለ። ሳሙኤልም እሴይን፥ “እርሱ እስኪመጣ ድረስ ለማዕድ አንቀመጥምና ልከህ አስመጣው” አለው።