ከዚህም ነገር በኋላ የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ እንዲህ ሲል፥ “አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ፤ ዋጋህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”
ዘፍጥረት 46:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፥ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ለእስራኤል ተናገረው። እርሱም “ምንድን ነው?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ሌሊት በራእይ ለእስራኤል ተገልጦ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፦ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ለእስራኤል ጠራው። እርሱም፦ “እነሆኝ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር፥ ሌሊት በራእይ ተገለጠለትና “ያዕቆብ! ያዕቆብ!” ብሎ ጠራው። እርሱም “አቤት ጌታ ሆይ፥ እነሆ አለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፦ ያዕቆብ ያዕቆብ ብሎ ለእስራኤል ተናገረው። እርሱም፦ እነሆኝ አለ። |
ከዚህም ነገር በኋላ የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ እንዲህ ሲል፥ “አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ፤ ዋጋህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”
እግዚአብሔርም አብራምን አለው፥ “ዘርህ ለእነርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመታትም ባሪያዎች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ ያሠቃዩአቸዋል፤ ያስጨንቋቸዋልም።
በዚያች ሌሊትም አቤሜሌክ ተኝቶ ሳለ እግዚአብሔር በሕልም ወደ እርሱ መጣ፤ እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ትሞታለህ፤ እርስዋ ባለ ባል ናትና።”
ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እንዲህ ሆነ። እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እንዲህም አለው፥ “አብርሃም! አብርሃም ሆይ፥” እርሱም፥ “እነሆ፥ አለሁ” አለ።
እግዚአብሔርንም መፍራት ባስተማረ በዘካርያስ ዘመን እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ልብ አደረገ፤ በዘመኑም እግዚአብሔርን ፈለገ፤ እግዚአብሔርም ነገሩን አከናወነለት።
እነሆም፥ አንድ ሰው በመጋላ ፈረስ ተቀምጦ በሌሊት አየሁ፥ እርሱም በሸለቆው ውስጥ ባሉ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ ነበር፣ በስተ ኋላውም መጋላና ሐመር አንባላይም ፈረሶች ነበሩ።
እርሱም፥ “ቃሌን ስሙ፤ በመካከላችሁ ለእግዚአብሔር ነቢይ የሆነ ቢኖር በራእይ እገለጥለታለሁ፤ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ።
“የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥ ተኝቶ ዐይኖቹ የተከፈቱለት እንዲህ ይላል፦
የእግዚአብሔር መልአክም በራእይ ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት በግልጥ ታየው፤ ወደ እርሱም ገብቶ፥ “ቆርኔሌዎስ ሆይ፥” አለው።
ለጳውሎስም በሌሊት አንድ መቄዶናዊ ሰው ቁሞ፥ “ወደ እኛ ወደ መቄዶንያ ዕለፍና ርዳን” እያለ ሲማልደው በራእይ ተገለጸለት።
በደማስቆም ስሙን ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታም በራእይ ተገልጦ፥ “ሐናንያ” ብሎ ጠራው፤ እርሱም፥ “አቤቱ፥ እነሆኝ” አለ።
እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፥ “ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፤ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።”