Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 9:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በደ​ማ​ስ​ቆም ስሙን ሐና​ንያ የሚ​ሉት አንድ ደቀ መዝ​ሙር ነበር፤ ጌታም በራ​እይ ተገ​ልጦ፥ “ሐና​ንያ” ብሎ ጠራው፤ እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ እነ​ሆኝ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በደማስቆ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታም በራእይ፣ “ሐናንያ!” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “ጌታ ሆይ፤ እነሆኝ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በደማስቆም ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀመዝሙር ነበረ፤ ጌታም በራእይ “ሐናንያ ሆይ!” አለው። እርሱም “ጌታ ሆይ! እነሆኝ፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በዚያን ጊዜ በደማስቆ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታ በራእይ “ሐናንያ!” ብሎ ጠራው፤ እርሱም “እነሆኝ ጌታ ሆይ!” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በደማስቆም ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ፥ ጌታም በራእይ፦ “ሐናንያ ሆይ፥” አለው። እርሱም፦ “ጌታ ሆይ፥ እነሆኝ” አለ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 9:10
23 Referencias Cruzadas  

“እንደ ሕጉም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሐና​ንያ የሚ​ባል አንድ ሰው ነበረ፤ በደ​ማ​ስ​ቆም የሚ​ኖሩ አይ​ሁድ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም በራ​እይ ከቀኑ በዘ​ጠኝ ሰዓት በግ​ልጥ ታየው፤ ወደ እር​ሱም ገብቶ፥ “ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ ሆይ፥” አለው።


ከእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሮች በኋላ እን​ዲህ ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ር​ሃ​ምን ፈተ​ነው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም ሆይ፥” እር​ሱም፥ “እነሆ፥ አለሁ” አለ።


የጌ​ታ​ንም ድምፅ፥ “ማንን እል​ካ​ለሁ? ማንስ ወደ​ዚያ ሕዝብ ይሄ​ድ​ል​ናል?” ሲል ሰማሁ? እኔም፥ “እነ​ሆኝ፥ ጌታዬ፥ እኔን ላከኝ” አልሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ሳሙ​ኤል! ሳሙ​ኤል” ብሎ ጠራው፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ይመ​ለ​ከት ዘንድ እንደ መጣ በአየ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከቍ​ጥ​ቋ​ጦው ውስጥ እር​ሱን ጠርቶ፥ “ሙሴ! ሙሴ!” አለው እር​ሱም፥ “ይህ ምን​ድን ነው?” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም፦ ‘ያዕ​ቆብ ያዕ​ቆብ’ አለኝ፤ እኔም፦ ‘እነ​ሆኝ ምን​ድን ነው?’ አል​ሁት።


በኋ​ለ​ኛ​ዪቱ ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ሥጋን በለ​በሰ ሁሉ ላይ ከመ​ን​ፈሴ አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችሁ ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ችሁ ራእ​ይን ያያሉ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሕል​ምን ያል​ማሉ።


ነገር ግን አል​ወ​ድ​ድ​ህም ቢለኝ፥ እነ​ሆኝ በፊቱ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ያድ​ር​ግ​ብኝ” አለው።


እር​ሱም፥ “ቃሌን ስሙ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ የሆነ ቢኖር በራ​እይ እገ​ለ​ጥ​ለ​ታ​ለሁ፤ ወይም በሕ​ልም እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ።


እር​ሱም ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ ጋር በሌ​ሊት ደረ​ሰ​ባ​ቸው፤ መታ​ቸ​ውም፤ በደ​ማ​ስቆ ግራ እስ​ካ​ለ​ች​ውም እስከ ሖባ ድረስ አሳ​ደ​ዳ​ቸው።


በዚ​ያም ሳያይ ሳይ​በ​ላና ሳይ​ጠጣ ሦስት ቀን ቈየ።


“በኢ​ዮጴ ከተማ ሳለሁ ስጸ​ልይ ተመ​ስጦ መጣ​ብ​ኝና ራእይ አየሁ፤ ታላቅ መጋ​ረጃ የመ​ሰለ ዕቃ በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ተይዞ ከሰ​ማይ ወረደ፤ ወደ እኔም መጣ።


ተከ​ት​ሎ​ትም ወጣ፤ ጴጥ​ሮስ ግን ራእይ የሚ​ያይ ይመ​ስ​ለው ነበረ እንጂ በመ​ል​አኩ የሚ​ደ​ረ​ገው ነገር እው​ነት እንደ ሆነ አላ​ወ​ቀም ነበር።


ለጳ​ው​ሎ​ስም በሌ​ሊት አንድ መቄ​ዶ​ናዊ ሰው ቁሞ፥ “ወደ እኛ ወደ መቄ​ዶ​ንያ ዕለ​ፍና ርዳን” እያለ ሲማ​ል​ደው በራ​እይ ተገ​ለ​ጸ​ለት።


ራእ​ዩ​ንም ባየ ጊዜ ወዲ​ያ​ውኑ ወደ መቄ​ዶ​ንያ ልን​ሄድ ወደ​ድን፤ ወን​ጌ​ልን እን​ሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጠ​ራን መስ​ሎ​ና​ልና።


ጌታ​ች​ንም ጳው​ሎ​ስን በሌ​ሊት ራእይ እን​ዲህ አለው፥ “አት​ፍራ፥ ነገር ግን ተና​ገር፥ ዝምም አት​በል፤


በደ​ማ​ስቆ ከተማ ከን​ጉሥ አር​ስ​ጣ​ስ​ዮስ በታች የሆነ የአ​ሕ​ዛብ አለቃ ሊይ​ዘኝ ወድዶ የደ​ማ​ስ​ቆን ከተማ ያስ​ጠ​ብቅ ነበር።


ከእኔ በፊት ወደ ነበ​ሩት ወደ ሐዋ​ር​ያ​ትም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አል​ወ​ጣ​ሁም፤ ነገር ግን ወደ ዐረብ ሀገር ሄድሁ፤ ዳግ​መ​ኛም ወደ ደማ​ስቆ ተመ​ለ​ስሁ።


ሳው​ልም በራ​እይ ሐና​ንያ የሚ​ባል ሰው ወደ እርሱ ገብቶ ያይ ዘንድ እጁን ሲጭ​ን​በት አየ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios