እነሆ፥ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበርና፥ እነሆ፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶዎች በዙርያ ከብበው እነሆ፥ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”
ዘፍጥረት 44:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳም አለ፦ “ለጌታችን ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይስ በምን እንነጻለን? እግዚአብሔር የአገልጋዮችህን ኀጢአት ገለጠ። እነሆ፥ እኛም ጽዋው ከእርሱ ዘንድ የተገኘበትም ደግሞ ለጌታችን አገልጋዮቹ ነን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁዳም፣ “ከእንግዲህ ለጌታችን ምን ማለት እንችላለን? ምንስ እንመልሳለን? እንዲህ ካለው በደል ንጹሕ መሆናችንን ማስረዳትስ እንዴት ይቻለናል? እግዚአብሔር የእኛን የአገልጋዮችህን በደል ገልጧል፤ ከእንግዲህ ጽዋው የተገኘበት ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ባሮችህ ነን” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሁዳም፥ “ከእንግዲህ ለጌታችን ምን ማለት እንችላለን? ምንስ እንመልሳለን? እንዲህ ካለው በደል ንጹሕ መሆናችንን ማስረዳትስ እንዴት ይቻለናል? እግዚአብሔር የእኛን የአገልጋዮችህን በደል ገልጦአል፤ ከእንግዲህ ጽዋው የተገኘበት ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ባሮችህ ነን” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁዳም “እንግዲህ ለጌታችን ምን መልስ እንሰጣለን? ራሳችንን ነጻ የምናደርግበት መልስ መስጠት ከቶ አንችልም፤ እግዚአብሔር የሠራነውን በደል ገልጦታል፤ እንግዲህ ዋንጫው የተገኘበት ሰው ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ባሪያዎችህ እንሁን” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳም አለ፦ ለጌታዬ ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይስ በምን እንነጻለን? እግዚአብሔር የባሪያዎችህን ኃጢአት ገለጠ እነሆ እኝም ጽዋው ከእርሱ ዘንድ የተገኘበቱም ደግሞ ለጌታዬ ባሪያዎቹ ነን። |
እነሆ፥ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበርና፥ እነሆ፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶዎች በዙርያ ከብበው እነሆ፥ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”
ደግሞም ሌላ ሕልምን አየ፤ ለአባቱና ለወንድሞቹም ነገራቸው፤ እንዲህም አለ፥ “እነሆ፥ ደግሞ ሌላ ሕልም አለምሁ፤ ሕልሙም እንዲህ ነው፦ ፀሐይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋክብትም ይሰግዱልኝ ነበር።”
ዮሴፍም አላቸው፥ “ይህን አደርግ ዘንድ አይገባኝም፤ ጽዋው የተገኘበት ሰው እርሱ አገልጋይ ይሁነኝ እንጂ፤ እናንተ ግን ወደ አባታችሁ በደኅና ሂዱ።”
እኔ አገልጋይህ በአባቴ ዘንድ ስለ ብላቴናው እንዲህ ብዬ ተውሼአለሁና፦ እርሱንስ ወደ አንተ መልሼ በፊትህ ባላቆመው በአባቴ ዘንድ በዘመናት ሁሉ ኀጢአተኛ እሆናለሁ።
እርስዋም ኤልያስን፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? አንተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?” አለችው።
አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው እኛ አምልጠን ቀርተናል፤ እነሆ በፊትህ በበደላችን አለን፤ ስለዚህ በፊትህ ሊቆም የሚችል የለም።”
“አንተ ስታስተምረኝ እኔ የምመልሰው ምን አለኝ? ይህንስ እየሰማሁ ከእግዚአብሔር ጋር እከራከር ዘንድ እኔ ምንድን ነኝ? እጄን በአፌ ላይ ከማኖር በቀር የምመልሰው ምንድን ነው?
ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፤ ይህም ኀጢአትን የማስወገድ ፍሬ ሁሉ ነው።
ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተከፈተ፤ ጴጥሮስንና ወንድሞቹ ሐዋርያትንም፥ “ወንድሞቻችን ሆይ፥ ምን እናድርግ?” አሏቸው።
የእስራኤል ልጆች ግን እርም በሆነው ነገር ታላቅ በደል በደሉ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ እርም ከሆነው ነገር ወሰደ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ልጆች ላይ ተቈጣ።
በዘንበሪም ወገን ምልክት ታየ፤ የዘንበሪም ቤተ ሰብ እያንዳንዱ ተለየ፤ ከይሁዳም ወገን በሆነ በከርሚ ልጅ በዘንበሪ ልጅ በዛራ ልጅ በአካን ላይ ምልክት ታየ።
አዶኒቤዜቅም፥ “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡ ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ በታች ፍርፋሪ ይለቅሙ ነበሩ፤ እኔ እንዳደረግሁ እግዚአብሔር እንዲሁ መለሰልኝ” አለ። ወደ ኢየሩሳሌምም ወሰዱት፥ በዚያም ሞተ።