Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 44:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “ይህን አደ​ርግ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ጽዋው የተ​ገ​ኘ​በት ሰው እርሱ አገ​ል​ጋይ ይሁ​ነኝ እንጂ፤ እና​ንተ ግን ወደ አባ​ታ​ችሁ በደ​ኅና ሂዱ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዮሴፍም፣ “ይህንስ ፈጽሞ አላደርገውም፤ ባሪያዬ የሚሆነው ጽዋው የተገኘበት ሰው ብቻ ነው፤ የቀራችሁት በሰላም ወደ አባታችሁ ተመለሱ” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዮሴፍም፥ “ይህንንስ ፈጽሞ አላደርገውም፤ ባርያዬ የሚሆነው ጽዋው የተገኘበት ሰው ብቻ ነው፤ የቀራችሁት በሰላም ወደ አባታችሁ ተመለሱ” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዮሴፍም “ይህንንስ ከቶ አላደርገውም! ዋንጫው የተገኘበት ሰው ብቻ የእኔ ባሪያ መሆን አለበት፤ ሌሎቻችሁ በሰላም ወደ አባታችሁ መመለስ ትችላላችሁ!” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እርሱም እላቸው፦ ይህን አደርግ ዘንድ አይሆንልኝም ጽዋው የተገኘበቱ ሰው እርሱ ባሪያ ይሁነኝ እናንተም ወደ አባታችሁ በደኅና ውጡ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 44:17
10 Referencias Cruzadas  

አቤቱ ይህ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም፤ ይህን ነገር አታ​ድ​ርግ፤ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ገዛ ይህን ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም።”


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር እንደ አለ በአ​የን ጊዜ በአ​ን​ተና በእኛ መካ​ከል መሐላ ይሁን፤ አንተ በእኛ ላይ ክፉ እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ፤ እኛም በአ​ንተ ላይ ክፉ እን​ዳ​ና​ደ​ርግ እን​ማ​ማ​ላ​ለን።”


በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ዮሴፍ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ትድኑ ዘንድ ይህን አድ​ርጉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈ​ራ​ለ​ሁና።


እር​ሱም አለ፥ “አሁ​ንም እን​ዲሁ እንደ ነገ​ራ​ችሁ ይሁን፤ ጽዋው የተ​ገ​ኘ​በት እርሱ ለእኔ አገ​ል​ጋይ ይሁ​ነኝ፤ እና​ን​ተም ንጹ​ሓን ትሆ​ና​ላ​ችሁ።”


ይሁ​ዳም አለ፦ “ለጌ​ታ​ችን ምን እን​መ​ል​ሳ​ለን? ምንስ እን​ና​ገ​ራ​ለን? ወይስ በምን እን​ነ​ጻ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን ኀጢ​አት ገለጠ። እነሆ፥ እኛም ጽዋው ከእ​ርሱ ዘንድ የተ​ገ​ኘ​በ​ትም ደግሞ ለጌ​ታ​ችን አገ​ል​ጋ​ዮቹ ነን።”


ይሁ​ዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በፊ​ትህ አን​ዲት ቃልን እን​ድ​ና​ገር እለ​ም​ና​ለሁ፤ እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን አት​ቈ​ጣኝ፤ አንተ ከፈ​ር​ዖን ቀጥ​ለህ ነህና።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ተና​ገረ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጠባቂ በም​ሳሌ እን​ዲህ አለኝ፦ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ታጸኑ ዘንድ፥ በሰ​ዎች መካ​ከል ተና​ገ​ርሁ፥”


በሀ​ገ​ሩም በሰ​ላም ኖረ፥ ማደ​ሪ​ያ​ውም በጽ​ዮን ነው፤


ኃጥኡን ጻድቅ፥ ጻድቁንም ኃጥእ ብሎ መፍረድ በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰና የተናቀ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos