ዘፍጥረት 42:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም አለ፥ “ልጄ ከእናንተ ጋር አይወርድም፤ ወንድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀርቶአልና፤ በምትሄዱበት መንገድ ምናልባት ክፉ ነገር ቢያገኘው ሽምግልናዬን በኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም፣ “ልጄ ዐብሯችሁ ወደዚያ አይወርድም፤ ወንድሙ እንደሆን ሞቷል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው። ይዛችሁት ስትሄዱ በመንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበት፣ ሽበቴን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም፥ “ልጄ አብሮአችሁ ወደዚያ አይወርድም፤ ወንድሙ እንደሆን ሞቷል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው። ይዛችሁት ስትሄዱ በመንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበት፥ ሽበቴን በመሪር ኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም “ምንም ቢሆን ከእናንተ ጋር አይሄድም፤ ወንድሙ ሞቶአል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው፤ በመንገድ አንድ ጒዳት ቢደርስበት በእርጅናዬ ዘመን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እንድወርድ ታደርጉኛላችሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም አለ፦ ልጅሴ ከእናንተ ጋር አይወርድም ወንድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀርቶአልና በምትሄዱበት መንገድ ምናልባት ክፋ ነገር ቢያገኘው ሽምግልናዬን በኅዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ። |
ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰብስበው መጡ። ኀዘኑንም ያስተዉት ዘንድ አባታቸውን ማለዱት። ኀዘኑንም መተውን እንቢ አለ፥ እንዲህም አላቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃብር እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም ስለ እርሱ አለቀሰ።
እነርሱም አሉ፥ “ባሪያዎችህ በከነዓን ምድር የምንኖር ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ ታናሹም እነሆ ዛሬ ከአባታችን ጋር ነው፤ ሌላውም ሞቶአል።”
ሮቤልም አባቱን አለው፥ “ወደ አንተ መልሼ ያላመጣሁት እንደሆነ ሁለቱን ልጆችን ግደል፤ ልጅህን በእጄ ስጠኝ፤ እኔም ወደ አንተ እመልሰዋለሁ።”
የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ግን ያዕቆብ ከወንድሞቹ ጋር አልሰደደውም፥ “ምናልባት ክፉ እንዳያገኘው” ብሎአልና።
እኛም ለጌታዬ እንዲህ አልን፦ ሽማግሌ አባት አለን፤ በሽምግልናው የወለደውም ታናሽ ብላቴና አለ፤ ወንድሙ ግን ሞተ፤ ለእናቱም እርሱ ብቻውን ቀረ፤ አባቱም ይወድደዋል።
እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበብንና ዕውቀትን፥ ደስታንም ይሰጠዋል፤ ለኀጢአተኛ ግን በእግዚአብሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ጥረትን ይሰጠዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፤ እስከ ሽበትም ድረስ እኔ ነኝ፤ እኔ እታገሣችኋለሁ፤ እኔ ሠርቻለሁ፤ እኔም ይቅር እላለሁ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፤ እኔም አድናችኋለሁ።