ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፤ ዔሳውም በልቡ አለ፥ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ትቅረብ፤ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
ዘፍጥረት 37:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ወደ እነርሱ ሳይቀርብ ከሩቅ አስቀድመው አዩት፥ ይገድሉትም ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞቹም ዮሴፍ ወደ እነርሱ ሲመጣ በሩቅ አዩት፤ ወደ ነበሩበትም ስፍራ ከመድረሱ በፊት ሊገድሉት ተማከሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም በሩቅ ሳለ አዩት፥ ወደ እነርሱም ገና ሳይቀርብ ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም በሩቅ አዩት፤ ወደ እነርሱም ከመድረሱ በፊት ሊገድሉት ተማከሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ በሩቅ ሳለ አዩት ወድ እነርሱም ገና ሳይቀርብ ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ። |
ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፤ ዔሳውም በልቡ አለ፥ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ትቅረብ፤ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
የዮሴፍም ወንድሞች አባታቸው እንደ ሞተ በአዩ ጊዜ እንዲህ አሉ፥ “ምናልባት ዮሴፍ ያደረግንበትን ክፋት ያስብብን ይሆናል፤ ባደረግንበትም ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል።”
እናንተ በእኔ ላይ ክፉ መከራችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲመገብ ለማድረግ ለእኔ መልካም መከረ።
ነፍሴንም የሚሹአት በረቱብኝ፥ መከራዬንም የሚፈልጉ ከንቱን ተናገሩ፥ ሁልጊዜም ያጠፉኝ ዘንድ በሽንገላ ይመክራሉ።
ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረ። የካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር።
በነጋም ጊዜ አይሁድ ተሰብስበው፥ ጳውሎስን እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተስማምተው ተማማሉ።
ሳኦልም ለልጁ ለዮናታንና ለብላቴኖቹ ሁሉ ዳዊትን ይገድሉ ዘንድ ነገራቸው። የሳኦል ልጅ ዮናታን ግን ዳዊትን እጅግ ይወድደው ነበር።