ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊው የብኤልን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊው የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፤
ዘፍጥረት 34:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለያዕቆብ የተወለደች የልያ ልጅ ዲናም የዚያን ሀገር ሴቶች ልጆችን ለማየት ወጣች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ሴት ልጅ ዲና፣ አንድ ቀን የዚያን አገር ሴቶች ለማየት ወጣች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የልያ ልጅ ዲናም፥ የዚያን አገር ሴት ልጆችን ለማየት ወጣች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዕለታት አንድ ቀን ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ዲና በዚያ አካባቢ የሚኖሩትን ከነዓናውያት ሴቶች ለማየት ወጣች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለያዕቆብ የወለደችለት የልያ ልጅ ዲናም የዚያን አገር ሴቶች ልጆችን ለማየት ወጣች። |
ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊው የብኤልን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊው የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፤
ርብቃም ይስሐቅን አለችው፥ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ከዚህ ሀገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለእኔ ምኔ ነው?”
ዔሳውም ይስሐቅ ያዕቆብን እንደ ባረከው በአየ ጊዜ ከዚያም ሚስትን ያገባ ዘንድ ወደ ሁለቱ የሶርያ ወንዞች መካከል እንደ ላከው፥ በባረከውም ጊዜ፥ “ከከነዓን ሴቶች ልጆች ሚስትን አታግባ” ብሎ እንዳዘዘው፥
ልያ በመስጴጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው፤ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ አራት ነፍስ ናቸው።
ከዚህም ጋር ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራን መፍታት ደግሞ ይማራሉ፤ የማይገባውንም እየተናገሩ ለፍላፊዎችና በነገር ገቢዎች ይሆናሉ እንጂ፥ ሥራ ፈቶች ብቻ አይደሉም።