Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ጢሞቴዎስ 5:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ከዚህም ጋር ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራን መፍታት ደግሞ ይማራሉ፤ የማይገባውንም እየተናገሩ ለፍላፊዎችና በነገር ገቢዎች ይሆናሉ እንጂ፥ ሥራ ፈቶች ብቻ አይደሉም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በተጨማሪም ሥራ መፍታትንና ከቤት ቤት መዞርን ይለምዳሉ፤ ሥራ ፈት መሆን ብቻ ሳይሆን፣ የማይገባውን እየተናገሩ ሐሜተኞችና በሰው ጕዳይም ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከዚህም ጎን ለጎን ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ ፈቶችም ብቻ ሳይሆኑ የማይገባቸውን እየተናገሩ ሰውን የሚያሙና በነገር ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ደግሞም ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ መፍታት ብቻ ሳይሆን በየሰዉ ቤት እየዞሩ ሰውን የሚያሙ፥ በሰው ነገር የሚገቡና መናገር የማይገባቸውን የሚናገሩ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ከዚህም ጋር ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራን መፍታት ደግሞ ይማራሉ፥ የማይገባውንም እየተናገሩ ለፍላፊዎችና በነገር ገቢዎች ይሆናሉ እንጂ፥ ሥራ ፈቶች ብቻ አይደሉም።

Ver Capítulo Copiar




1 ጢሞቴዎስ 5:13
14 Referencias Cruzadas  

ሁለት ምላስ የሆነ ሰው የጉባኤን ምሥጢር ይገልጣል፤ በአንደበቱ የታመነ ግን ነገርን ይሰውራል።


ዘዋሪ ሐሜተኛ ምሥጢርን ይገልጣል፤ በከንፈሩ የሚያባብል ሰውን አትገናኘው።


ሁከተኛና አበያ ናት፥ እግሮችዋም በቤቷ አያርፉም፥


በሕ​ዝ​ብህ መካ​ከል በሸ​ን​ጋ​ይ​ነት አት​ዙር፤ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህም ደም ላይ አት​ቁም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝ።


በዚ​ያም ቤት ተቀ​መጡ፤ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ገ​ኘ​ው​ንም ብሉ፥ ጠጡም፤ ለሠ​ራ​ተኛ ዋጋው ይገ​ባ​ዋ​ልና፤ ከቤ​ትም ወደ ቤት አት​ሂዱ።


በጉ​ባ​ኤም ሆነ በቤት ስነ​ግ​ራ​ች​ሁና ሳስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ከሚ​ጠ​ቅ​ማ​ችሁ ነገር አን​ዳች ስን​ኳን አላ​ስ​ቀ​ረ​ሁ​ባ​ች​ሁም።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ወደ እነ​ርሱ ይመ​ልሱ ዘንድ ጠማማ ትም​ህ​ር​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሰዎች ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ይነ​ሣሉ።


የፊተኛውንም እምነታቸውን ስለ ናቁ ይፈረድባቸዋል፤


እነዚህም ስለ ነውረኛ ረብ የማይገባውን እያስተማሩ ቤቶችን በሞላው ስለ ሚገለብጡ፥ አፋቸውን መዝጋት ይገባል።


ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ! ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።


ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጉዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤


ስለዚህ እኔ ብመጣ፥ በእኛ ላይ በክፉ ቃል እየለፈለፈ የሚያደርገውን ሥራውን አሳስባለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም፤ ሊቀበሉአቸውም የሚወዱትን ከልክሎ ከቤተ ክርስቲያን ያወጣቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos