ፈርዖንም አብራምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደረግህብኝ ምንድን ነው? እርስዋ ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልገለጥህልኝም?
ዘፍጥረት 31:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም ያዕቆብን አለው፥ “ለምን እንዲህ አደረግህ? ከእኔ በስውር የኰበለልህ? ልጆችንስ ሰርቀህ በሰይፍ እንደማረከ የወሰድኻቸው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “ምን ማድረግህ ነው? አታልለኸኛል፤ ልጆቼን የጦር ምርኮኛ ይመስል አካልበህ ወሰድሃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባም ያዕቆብን አለው፥ “የፈጸምከው ምንድነው? እኔን አታልልከኝ፥ ልጆቼንስ እንደ ሰይፍ ምርኮኛ ለምን ወሰድካቸው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “ስለምን እንዲህ አድርገህ አታለልከኝ? ሴቶች ልጆቼንስ በጦርነት እንደ ተማረኩ ያኽል ይዘሃቸው ለምን ሄድክ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም ያዕቆብን አለው፦ ለምን እንዲህ አደረግህ? ከእኔ ከድተህ ኮበለልህ ልጆቼንም በሰይፍ እንደ ተማረኩ ዓይነት ነዳሃቸው። |
ፈርዖንም አብራምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደረግህብኝ ምንድን ነው? እርስዋ ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልገለጥህልኝም?
አቤሜሌክም አለ፥ “ይህ ያደረግህብን ምንድን ነው? ከሕዝቡ አንዱ ባለማወቅ ከሚስትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት በቀረው ነበር፤ ኀጢአትንም ልታመጣብን ነበር።”
በነጋም ጊዜ እነሆ ልያ ነበረች፤ ያዕቆብም ላባን፥ “ምነው እንደዚህ አደረግህብኝ? ያገለገልሁህ ስለ ራሔል አልነበረምን? ለምን አታለልኸኝ?” አለው።
ስለዚህም እግዚአብሔር ከአባታችን የነሣው ይህ ሁሉ ሀብትና ክብር ለእኛና ለልጆቻችን ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ያለህን ሁሉ አድርግ።”
ላባም ያዕቆብን አገኘው፤ ያዕቆብም ድንኳኑን በተራራው ላይ ተክሎ ነበር፤ ላባም ወንድሞቹን በገለዓድ ተራራ አስቀመጣቸው።
ያዕቆብም ተቈጣ፤ ላባንም ወቀሰው፤ ያዕቆብም መለሰ፤ ላባንም እንዲህ አለው፥ “የበደልሁህ በደል ምንድን ነው? ኀጢአቴስ ምንድን ነው? ይህን ያህል ያሳደድኸኝ?
ጲላጦስም መልሶ፥ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ ወገኖችህና ሊቃነ ካህናት አይደሉምን? Aረ ምን አድርገሃል?” አለው።
ኢያሱም አካንን፥ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ፤ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝም” አለው።
ሳኦልም ዮናታንን፥ “ያደረግኸውን ንገረኝ” አለው፤ ዮናታንም፥ “በእጄ ባለው በበትሬ ጫፍ ጥቂት ማር በርግጥ ቀምሻለሁ፤ እነሆኝ፥ እሞታለሁ” ብሎ ነገረው።
ሴቶቹንና በውስጥዋም የነበሩትን ሁሉ ከታናሽ እስከ ታላቅ ድረስ ማርከው ነበር፤ ሁሉንም ወስደው መንገዳቸውን ሄዱ እንጂ ሴቶችንም ሆነ ወንዶችን አልገደሉም።