Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 31:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ላባም ያዕቆብን አለው፥ “የፈጸምከው ምንድነው? እኔን አታልልከኝ፥ ልጆቼንስ እንደ ሰይፍ ምርኮኛ ለምን ወሰድካቸው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከዚያም ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “ምን ማድረግህ ነው? አታልለኸኛል፤ ልጆቼን የጦር ምርኮኛ ይመስል አካልበህ ወሰድሃቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ከዚህ በኋላ ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “ስለምን እንዲህ አድርገህ አታለልከኝ? ሴቶች ልጆቼንስ በጦርነት እንደ ተማረኩ ያኽል ይዘሃቸው ለምን ሄድክ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ላባም ያዕ​ቆ​ብን አለው፥ “ለምን እን​ዲህ አደ​ረ​ግህ? ከእኔ በስ​ውር የኰ​በ​ለ​ልህ? ልጆ​ች​ንስ ሰር​ቀህ በሰ​ይፍ እን​ደ​ማ​ረከ የወ​ሰ​ድ​ኻ​ቸው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ላባም ያዕቆብን አለው፦ ለምን እንዲህ አደረግህ? ከእኔ ከድተህ ኮበለልህ ልጆቼንም በሰይፍ እንደ ተማረኩ ዓይነት ነዳሃቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 31:26
17 Referencias Cruzadas  

ሴቶቹን፥ በዚያ የነበሩትን ወጣቶችና ሽማግሌዎቹን ሁሉ ማርከው ወሰዱ፤ የማረኩትንም ይዘው ከመሄድ በስተቀር አንዱንም አልገደሉም ነበር።


ዳዊትም፥ “እኔ ምን አደረግሁ? መጠየቅ እንኳ አልችልምን?” አለ።


ከዚያም ሳኦል ዮናታንን፥ “ያደረግኸውን ነገር ንገረኝ” አለው። ዮናታንም፥ “በበትሬ ጫፍ ጥቂት ማር ቀምሻለሁ፤ እነሆኝ፥ ለመሞት ዝግጁ ነኝ” አለው።


ኢያሱም አካንን እንዲህ አለው፦ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ክብር ስጥ፥ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝ።”


ሀብታቸውን ሁሉ ሕፃናቶቻቸውንና ሴቶቻቸውንም ሁሉ ማረኩ፥ በቤት ያለውንም ሁሉ ዘረፉ።


ያዕቆብም ተቆጣ ላባንም ወቀሰው፥ ያዕቆብም ላባንም እንዲህ አለው፥ “ምን በደልሁህ? ይህን ያህል ያሳደድኸኝ፥ ኃጢአቴስ ምንድነው?


ስለዚህም እግዚአብሔር ከአባታችን የነሣው ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው፥ እንግዲያውስ አሁንም፥ እግዚአብሔር ያለህን ሁሉ፥ አድርግ።”


አቢሜሌክም አለ፦ “ይህ ያደረግህብን ምንድነው? ከሕዝብ አንዱ ከሚስትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት በቀረው ነበር፥ ኃጢአትንም ልታመጣብን ነበር።”


ፈርዖንም አብራምን ጠርቶ አለው፦ ይህ ያደረግህብኝ ምንድነው? እርሷ ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልገለጥህልኝም?


ጌታም ቃየልን እንዲህ አለው፥ “ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል።


ጌታ እግዚአብሔርም ሴቲቱን፦ “ይህ ያደረግሽው ምንድነው?” አላት። ሴቲቱም፥ “እባብ አሳተኝና በላሁ” አለች።


ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይተባበራል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ።


ጲላጦስ መልሶ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ወገኖችህና የካህናት አለቆች ለእኔ አሳልፈው ሰጡህ፤ ምን አድርገሃል?” አለው።


ላባም ያዕቆብን ደረሰበት፤ ያዕቆብም ድንኳኑን ኮረብታማው አገር ተክሎ ነበር፥ ላባም ከዘመዶቹ ጋር በገለዓድ ኮረብታማው አገር ድንኳኑን ተከለ።


ስለምን በስውር ሸሸህ፥ እኔንም አታለልከኝ፥ በደስታና በዘፈንም በከበሮና በበገና እንድሰድድህ ለምን አልነገርኸኝም?


በነጋም ጊዜ እነሆ ልያ ሆና ተገኘች፥ ላባንም፦ “ምነው እንደዚህ አደረግህብኝ? ያገለግልሁህ ስለ ራሔል አልነበረምን? ለምን አታለልኸኝ?” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios