“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
ዘፍጥረት 28:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም ያዕቆብን ጠራው፤ ባረከውም፥ እንዲህም ብሎ አዘዘው፥ “ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች ሚስትን አታግባ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅ ያዕቆብን አስጠርቶ ከመረቀው በኋላ፣ እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ምንም ቢሆን ከነዓናዊት ሴት አታግባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም ያዕቆብን ጠራው፥ ባረከውም፥ እንዲህ ብሎም አዘዘው፦ “ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች ሚስትን አታግባ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይስሐቅ ያዕቆብን ጠርቶ መረቀው፤ እንዲህም ሲል አዘዘው፤ “ከነዓናዊት ሴት እንዳታገባ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይስሐቅም ያዕቆብን ጠራው ባረከውም እንዲህ ብሎም አዘዘው፤ |
“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
ርብቃም ይስሐቅን አለችው፥ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ከዚህ ሀገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለእኔ ምኔ ነው?”
ዔሳውም ይስሐቅ ያዕቆብን እንደ ባረከው በአየ ጊዜ ከዚያም ሚስትን ያገባ ዘንድ ወደ ሁለቱ የሶርያ ወንዞች መካከል እንደ ላከው፥ በባረከውም ጊዜ፥ “ከከነዓን ሴቶች ልጆች ሚስትን አታግባ” ብሎ እንዳዘዘው፥
ሴቶች ልጆቻችንንም እንሰጣችኋለን፤ የእናንተንም ሴቶች ልጆች ለሚስትነት እንወስዳለን፤ አንድ ሕዝብም ሆነን ከእናንተ ጋር እንኖራለን።
ያዕቆብም ባረካቸው፤ እንዲህም አለ፥ “አባቶች አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ ደስ ያሰኙት እርሱ እግዚአብሔር፥ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፥
እነዚህም ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች ናቸው፤ አባታቸውም ይህን ነገር ነገራቸው፤ ባረካቸውም፤ እያንዳንዳቸውንም እንደ በረከታቸው ባረካቸው።
የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ፤ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም አጋቡ፤ እነርሱም ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ይውለዱ፤ ከዚያም ተባዙ፤ ጥቂቶችም አትሁኑ።
ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ሙሴ በባሳን ውስጥ ርስት ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለቀረው ለእኩሌታው ግን ኢያሱ በዮርዳኖስ ማዶ በባሕር በኩል በወንድሞቻቸው መካከል ርስት ሰጣቸው። ኢያሱም ወደ ቤታቸው በአሰናበታቸው ጊዜ እንዲህ ብሎ መረቃቸው፦