ታራም ልጁን አብራምንና የልጅ ልጁን የአራንን ልጅ ሎጥን፥ የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ምድር አወጣቸው። ወደ ካራንም መጡ፤ በዚያም ተቀመጡ።
ዘፍጥረት 27:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ስማ፤ ተነሣና በሶርያ ወንዞች መካከል ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሂድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ልጄ ሆይ፤ እኔ የምልህን አድርግ፤ በካራን ምድር ወደሚኖረው ወደ ላባ ቶሎ ሽሽ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ልጄ ሆይ ቃሌን ስማ፥ ተነሣና ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሂድ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁንም ልጄ ሆይ፥ የምልህን አድርግ፤ ተነሥተህ በካራን ወደሚኖረው ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሽሽ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ልጄ ሆይ ቃሌን ስማ ተነሣና ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሂድ፤ |
ታራም ልጁን አብራምንና የልጅ ልጁን የአራንን ልጅ ሎጥን፥ የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ምድር አወጣቸው። ወደ ካራንም መጡ፤ በዚያም ተቀመጡ።
ይስሐቅም ሚስት ትሆነው ዘንድ የሶርያዊውን የላባን እኅት፥ የሶርያዊውን የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ከሁለቱ ከሶርያ ወንዞች መካከል በወሰዳት ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር።
ለርብቃም ታላቁ ልጅዋ ዔሳው ያለው ተነገራት፤ ታናሹን ልጅዋን ያዕቆብንም ልካ ጠራችው፤ አለችውም፥ “እነሆ ወንድምህ ዔሳው ያድድንሃል፤ ሊገድልህም ይፈልጋል።
ይስሐቅም ልጁ ያዕቆብን ላከው፤ እርሱም የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም የሚሆን የሶርያዊው ባቱኤል ልጅ ላባ ወዳለበት ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል ሄደ።
እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው፥ “ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፤ በዚያም ኑር፤ ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጥሁልህ ለእኔ መሥውያን ሥራ።”
የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ልጆቹ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ ያዘዛቸው ቃል ተፈጸመ፤ ለአባታቸውም ትእዛዝ ታዝዘዋልና እስከ ዛሬ ድረስ ወይን አይጠጡም፤ እኔም በማለዳ ስለ እናንተ ተናገርሁ፤ ሆኖም አልሰማችሁኝም።