ለአብራምም ስለ እርስዋ መልካም አደረጉለት፤ ለእርሱ በጎችም፥ በሬዎችም፥ አህዮችም፥ በቅሎዎችም፥ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችም፥ ግመሎችም ነበሩት።
ዘፍጥረት 14:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብራምም የወንድሙ ልጅ ሎጥ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ ወገኖቹንና ቤተሰቦቹን ሁሉ ቈጠራቸው፤ እነርሱም ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ሆኑ፤ እስከ ዳን ድረስ ተከትሎ አሳደዳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራም የወንድሙን ልጅ መማረክ እንደ ሰማ በቤቱ ተወልደው አድገው የሠለጠኑ 318 ጦረኞች አሰልፎ እስከ ዳን ድረስ ገሠገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብራምም ወንድሙ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ የተወለዱትን ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ብላቴኖቹን አሰለፈ፥ ፍለጋቸውንም ተከትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብራም የወንድሙ ልጅ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ ተወልደው የጦር ልምምድ ያላቸውን 318 ሰዎች በትጥቅ አደራጅቶ አራቱን ነገሥታት በመከታተል እስከ ዳን ድረስ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብራምም ወንድሙ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ የተወለዱትን ሦስት መቶ አሥራ ስምንት ብላቴኖቹን አሰለፈ፥ ፍለጋቸውንም ተለትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ። |
ለአብራምም ስለ እርስዋ መልካም አደረጉለት፤ ለእርሱ በጎችም፥ በሬዎችም፥ አህዮችም፥ በቅሎዎችም፥ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችም፥ ግመሎችም ነበሩት።
አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፤ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ።
ሕፃኑንም በስምንተኛው ቀን ትገርዙታላችሁ፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ፥ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ።
አብርሃምም ልጁን ይስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ፥ በወርቅም የገዛውን ወንድ ሁሉ፥ ከቤተ ሰቡም ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ። የሥጋቸውንም ቍልፈት እግዚአብሔር እንዳለው በዚያው ቀን ገረዘ።
ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።”
“አይሆንም፥ ጌታ ሆይ፥ ስማን፤ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእኛ ንጉሥ ነህና ከመቃብር ስፍራችን በመረጥኸው ቦታ ሬሳህን ቅበር፤ ሬሳህን በዚያ ትቀብር ዘንድ ከእኛ መቃብሩን የሚከለክልህ የለም።”
ወልደ አዴርም ለንጉሡ ለአሳ እሺ አለው፤ የሠራዊቱንም አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ ሰድዶ ኢናንንና ዳንን፥ አቤልቤትመዓካንና ኬኔሬትን ሁሉ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ መታ።
ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችን ገዛሁ፤ በቤት የተወለዱ አገልጋዮችም ነበሩኝ፤ ከእኔ አስቀድመው በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ብዙ የበጎችና የከብቶች መንጋዎች ነበሩኝ።
ሙሴም ከሞዓብ ሜዳ በኢያሪኮ ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስ ወጣ፤ እግዚአብሔርም እስከ ዳን ድረስ ያለውን የገለዓድን ምድር አሳየው፤
ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።
ከተማዪቱንም ከእስራኤል በተወለደው በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት፤ የከተማዪቱም ስም አስቀድሞ ሌሳ ነበረ።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅበሩም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፥ ከገለዓድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ።
ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች፥ ከወሰዱት ምርኮ ሁሉ፥ ታላቅም ሆነ፥ ታናሽም ሆነ፥ ምንም የተወላቸው የለም፤ ዳዊትም ሁሉን አስጣለ።