Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 23:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “አይ​ሆ​ንም፥ ጌታ ሆይ፥ ስማን፤ አንተ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ለእኛ ንጉሥ ነህና ከመ​ቃ​ብር ስፍ​ራ​ችን በመ​ረ​ጥ​ኸው ቦታ ሬሳ​ህን ቅበር፤ ሬሳ​ህን በዚያ ትቀ​ብር ዘንድ ከእኛ መቃ​ብ​ሩን የሚ​ከ​ለ​ክ​ልህ የለም።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ስማን ጌታዬ፤ አንተ እኮ በእኛ ዘንድ እንደ ኀያል መስፍን ነህ፤ ከመቃብር ቦታችን በመረጥኸው ስፍራ ሬሳህን መቅበር ትችላለህ፤ ማንኛችንም ብንሆን የሞተብህን ሰው እንዳትቀብርበት የመቃብር ቦታችንን አንከለክልህም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “ጌታዬ ሆይ፥ እስቲ ስማን፤ አንተ በመካከላችን እንደ ታላቅ መስፍን ነህ፤ ከመቃብሮቻችን ጥሩውን መርጠህ ሬሳህን እዚያ ቅበር፤ ሬሳህን ትቀብር ዘንድ ከእኛ መቃብሩን የሚከለክልህ የለም።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “ጌታው፥ እስቲ ስማን፤ አንተ በመካከላችን እንደ ታላቅ መስፍን ነህ፤ ከመቃብሮቻችን ጥሩውን መርጠህ የሚስትህን አስከሬን እዚያ ቅበር፤ ሁላችንም ብንሆን የሚስትህን አስከሬን የምትቀብርበት መቃብር ልንሰጥህ ፈቃደኞች ነን” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አሉትም፦ ጌታ ሆይ ስማን፤ አንተ በእኛ መካከለ ከእግዚአብሔር አለቃ ነህ ከመቃብር ስፍራችን በመልካሙ ቦታ ሬሳህን ቅበር፤ ሬሳህን ትቀብር ዘንድ ከእኛ መቃብሩን የሚከለክልህ የለም።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 23:6
19 Referencias Cruzadas  

አብ​ራ​ምም በከ​ብት፥ በብ​ርና በወ​ርቅ እጅግ በለ​ጸገ።


አብ​ራ​ምም የወ​ን​ድሙ ልጅ ሎጥ እንደ ተማ​ረከ በሰማ ጊዜ ወገ​ኖ​ቹ​ንና ቤተ​ሰ​ቦ​ቹን ሁሉ ቈጠ​ራ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሦስት መቶ ዐሥራ ስም​ንት ሆኑ፤ እስከ ዳን ድረስ ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ዳ​ቸው።


ሣራም ለብ​ቻዋ በል​ብዋ እን​ዲህ ስትል ሳቀች፥ “እስከ ዛሬ ገና ነኝን? ጌታ​ዬም ፈጽሞ ሽም​ግ​ሎ​አል።”


አሁ​ንም የሰ​ው​የ​ውን ሚስት መልስ፤ ነቢይ ነውና፥ ስለ አን​ተም ይጸ​ል​ያል፤ ትድ​ና​ለ​ህም። ባት​መ​ል​ሳት ግን አንተ እን​ድ​ት​ሞት፥ ለአ​ንተ የሆ​ነ​ውም ሁሉ እን​ዲ​ሞት በር​ግጥ ዕወቅ።”


በዚያ ዘመን አቤ​ሜ​ሌክ፥ ሚዜው አኮ​ዘ​ትና የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ፋኮል ወደ አብ​ር​ሃም ሄደው አሉት፥ “በም​ታ​ደ​ር​ገው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤


የኬጢ ልጆ​ችም ለአ​ብ​ር​ሃም መለሱ፤ አሉ​ትም፦


አብ​ር​ሃ​ምም ተነሣ፤ በሀ​ገሩ ሕዝብ ፊትም ለኬጢ ልጆች ሰገደ።


እር​ስ​ዋም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ጠጣ” አለ​ችው፤ ፈጥ​ናም እን​ስ​ራ​ዋን ከጫ​ን​ቃዋ በእ​ጅዋ አው​ርዳ እስ​ኪ​ረካ አጠ​ጣ​ችው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌታ​ዬን እጅግ ባረ​ከው፤ አገ​ነ​ነ​ውም፤ ላሞ​ች​ንና በጎ​ችን፥ ወር​ቅ​ንና ብርን፥ ወን​ዶች ባሪ​ያ​ዎ​ች​ንና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችን፥ ግመ​ሎ​ች​ንና አህ​ዮ​ች​ንም ሰጠው።


እር​ስ​ዋም አባ​ቷን፥ “ጌታዬ በፊ​ትህ ለመ​ቆም ስላ​ል​ቻ​ልሁ የአ​ቀ​ለ​ል​ሁህ አይ​ም​ሰ​ልህ፤ በሴ​ቶች የሚ​ደ​ርስ ግዳጅ ደር​ሶ​ብ​ኛ​ልና” አለ​ችው። ላባም የራ​ሔ​ልን ድን​ኳን በረ​በረ፤ ነገር ግን ጣዖ​ቶ​ቹን አላ​ገ​ኘም።


በዚያ ጊዜ አንተ፦ ‘ለጌ​ታዬ ለዔ​ሳው እጅ መንሻ የላ​ከው የአ​ገ​ል​ጋ​ይህ የያ​ዕ​ቆብ ነው፤ እር​ሱም ደግሞ እነሆ ከኋ​ላ​ችን ተከ​ት​ሎ​ናል’ በለው።”


እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ጌታ ሆይ፥ አይ​ደ​ለም፤ ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህስ ስንዴ ሊገዙ መጥ​ተ​ዋል፤


ጌታዬ የሚ​ጠ​ጣ​በ​ትን፥ ምስ​ጢ​ር​ንም የሚ​ያ​ው​ቅ​በ​ትን የብር ጽዋ ለምን ሰረ​ቃ​ችሁ? ባደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ነገር በደ​ላ​ችሁ።”


በየ​ዓ​ይ​በ​ታ​ችን አፍ ያገ​ኘ​ነ​ውን ብር እን​ኳን ይዘን ከከ​ነ​ዓን ሀገር ወደ አንተ ተመ​ል​ሰ​ናል፤ ከጌ​ታ​ህስ ቤት ወርቅ ወይስ ብር እን​ዴት እን​ሰ​ር​ቃ​ለን?


አሮ​ንም እን​ዲህ አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእኔ ላይ አት​ቈጣ፤ የዚ​ህን ሕዝብ ጠባይ አንተ ታው​ቃ​ለህ።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ግብ​ፅና የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ዶች ደከሙ፤ ቁመተ ረዥ​ሞች የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም ይገ​ዙ​ል​ሃል፤ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ታስ​ረው በኋ​ላህ ይከ​ተ​ሉ​ሃል፤ በፊ​ት​ህም ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም እየ​ሰ​ገዱ፦ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ ከእ​ር​ሱም ሌላ አም​ላክ የለም ብለው ይለ​ም​ኑ​ሃል።


እርስዋም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ከባሪያዎችህ እንደ አንዲቱ ሳልሆን አጽናንተኽኛልና፥ የባሪያህንም ልብ ደስ አሰኝተሃልና በዓይንህ ሞገስ ላግኝ አለችው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos