Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 15:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ወልደ አዴ​ርም ለን​ጉሡ ለአሳ እሺ አለው፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞች ላይ ሰድዶ ኢና​ን​ንና ዳንን፥ አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካ​ንና ኬኔሬ​ትን ሁሉ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ መታ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ቤን ሃዳድም የንጉሥ አሳን ሐሳብ ተቀብሎ፣ የጦር አዛዦቹን በእስራኤል ከተሞች ላይ አዘመተ፤ እርሱም ዒዮንን፣ ዳንን፣ አቤል ቤት ማዕካን እንዲሁም ንፍታሌምን ጨምሮ ኪኔሬትን በሙሉ ድል አድርጎ ያዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ንጉሥ ቤንሀዳድም አሳ ባቀረበው ሐሳብ ተስማምቶ የጦር አዛዦቹንና ሠራዊቱን በመላክ በእስራኤል ከተሞች ላይ አደጋ እንዲጥሉ አደረገ፤ እነርሱም ዒዮን፥ ዳን፥ አቤልቤትማዕካና የገሊላ ባሕር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች በገሊላ ባሕር አጠገብ የሚገኘውን አገርና የንፍታሌምን ግዛት ሁሉ ያዙ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ንጉሥ ቤንሀዳድም አሳ ባቀረበው ሐሳብ ተስማምቶ የጦር አዛዦቹንና ሠራዊቱን በመላክ በእስራኤል ከተሞች ላይ አደጋ እንዲጥሉ አደረገ፤ እነርሱም ዒዮን፥ ዳን፥ አቤልቤትማዕካና የገሊላ ባሕር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች በገሊላ ባሕር አጠገብ የሚገኘውን አገርና የንፍታሌምን ግዛት ሁሉ ያዙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ቤንሀዳድም ለንጉሡ ለአሳ እሺ አለው፤ የሠራዊቱንም አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ ሰድዶ ዒዮንንና ዳንን፥ አቤልቤት መዓካንና ኪኔሬትን ሁሉ የንፍታሌምንም አገር ሁሉ መታ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 15:20
10 Referencias Cruzadas  

በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በፋ​ቁሔ ዘመን የአ​ሶር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መጣ፤ ኢዮ​ንና አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካን፥ ያኖ​ዋ​ንም፥ ቃዴ​ስ​ንና አሶ​ር​ንም፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ገሊ​ላ​ንም፥ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶ​ርም አፈ​ለ​ሳ​ቸው።


ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል በተ​ወ​ለ​ደው በአ​ባ​ታ​ቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩ​አት፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ስም አስ​ቀ​ድሞ ሌሳ ነበረ።


በመ​ስ​ዕም በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ፥ በከ​ነ​ሬ​ትም ዐዜብ በዓ​ረባ፥ በቆ​ላ​ውም ባለ በፊ​ና​ዶር ሸለቆ ወደ ነበሩ ነገ​ሥ​ታት፥


አን​ዱን በቤ​ቴል ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም በዳን አኖረ።


በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ያለ​ውን ዓረባ እስከ ኬኔ​ሬት ባሕር ድረስ፥ በአ​ሴ​ሞት መን​ገድ አጠ​ገብ እስ​ካ​ለው እስከ ዓረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደ​ቡ​ብም በኩል ከፋ​ስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለ​ውን ምድር የገ​ዛው የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ ሴዎን፤


አብ​ራ​ምም የወ​ን​ድሙ ልጅ ሎጥ እንደ ተማ​ረከ በሰማ ጊዜ ወገ​ኖ​ቹ​ንና ቤተ​ሰ​ቦ​ቹን ሁሉ ቈጠ​ራ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሦስት መቶ ዐሥራ ስም​ንት ሆኑ፤ እስከ ዳን ድረስ ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ዳ​ቸው።


ለኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ለና​ቡቴ በሰ​ማ​ርያ ንጉሥ በአ​ክ​ዓብ ቤት አጠ​ገብ የወ​ይን ቦታ ነበ​ረው።


የን​ፍ​ታ​ሌም ልጆች ነገድ ርስት እነ​ዚህ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios