ገላትያ 2:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ተገለጠልኝም ወጣሁ፤ በከንቱ እንዳልሮጥ፥ ወይም በከንቱ ሮጬ እንዳልሆነ፥ በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል አለቆች መስለው ለሚታዩት አስታወቅኋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካገኘሁትም መገለጥ የተነሣ ወደዚያ ሄድሁ፤ በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል ለእነርሱም ገለጥሁላቸው። ይሁን እንጂ፣ ምናልባት በከንቱ እየሮጥሁ ወይም ሮጬ እንዳይሆን በመሥጋት፣ ዋነኞች ለሚመስሉት ብቻ በግል ይህን አስታወቅኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ተገለጠልኝም ወጣሁ፤ ምናልባትም በከንቱ እንዳልሮጥ ወይም ሮጬ እንዳልሆን፥ በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል፥ በመሪነታቸው ለታወቁት ለብቻቸው አስታወቅኋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሄድኩትም እግዚአብሔር በገለጠልኝ መሠረት ነው። ከዚህ በፊት የሠራሁትም ሆነ አሁን የምሠራው ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር በማለት ለአሕዛብ የምሰብከውን ወንጌል ታላላቅ ለሆኑት መሪዎች በግል አስታወቅኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ተገለጠልኝም ወጣሁ፤ ምናልባትም በከንቱ እንዳልሮጥ ወይም በከንቱ ሮጬ እንዳልሆን በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል አስታወቅኋቸው፤ ዋኖች ግን መስለው ለሚታዩ ለብቻቸው አስታወቅኋቸው። |
ያንጊዜም ሕዝቡ ሁሉ ጸጥ ብለው እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያደረገላቸውን ተአምራትና ድንቅ ሥራ ሁሉ ሲናገሩ ጳውሎስንና በርናባስን አዳመጡአቸው።
ሕዝቡም እጅግ ታወኩ፤ ጳውሎስንና በርናባስንም ተከራከሩአቸው፤ ስለዚህ ነገርም ጳውሎስንና በርናባስን፥ ጓደኞቻቸውንም በኢየሩሳሌም ወደ አሉት ወደ ሐዋርያትና ቀሳውስት ሊልኳቸው ተማከሩ።
ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜም ምእመናንና ሐዋርያት፥ ቀሳውስትም ተቀበሉአቸው፤ እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ያደረገላቸውን ነገሩአቸው።
በሁለተኛዪቱም ሌሊት ጌታችን ለጳውሎስ ተገልጦ፥ “ጽና፥ በኢየሩሳሌም ምስክር እንደ ሆንኸኝ እንዲሁ በሮም ምስክር ትሆነኛለህ” አለው።
በሸንጎዉም በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ የከበረ የኦሪት መምህር ስሙን ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ ተነሣ፤ ሐዋርያትንም ከጉባኤዉ ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ።
በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሽቀዳደሙ ሁሉ እንደሚፋጠኑ አታውቁምን? ለቀደመው የሚደረግለት ዋጋ አለ፤ እንዲሁ እናንተም እንድታገኙ ፈጽማችሁ ሩጡ።
በስሙም ለአሕዛብ ወንጌልን አስተምር ዘንድ፥ በእጄም የልጁ ክብር ይታወቅ ዘንድ ልጁን ገለጠልኝ፤ ያንጊዜም ከሥጋዊና ከደማዊ ሰው ጋር አልተማከርሁም።
አለቆች የመሰሉት ግን ቀድሞ እነርሱ እንዴት እንደ ነበሩ ልናገር አያገደኝም፤ እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና፤ አለቆች የመሰሉትም ከራሳቸው ምንም ነገር የጨመሩልኝ የለምና።
የሰጠኝንም ጸጋ ዐውቀው አዕማድ የሚሏቸው ያዕቆብና ኬፋ፥ ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ፥ እነርሱም ወደ አይሁድ እንድንሄድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን።
የሕይወትን ቃል እያስተማራችሁ፤ ክርስቶስ በሚመጣበት ቀን እኔ እንድመካ፤ የሮጥሁ በከንቱ አይደለምና፤ የደከምሁም በከንቱ አይደለምና።
ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደ ፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ “ፈታኝ ምናልባት ፈትኖአቸዋል፤ ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል፤” ብዬ እምነታችሁን ለማወቅ ላክሁ።
እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ፥ የኀጢአትንም ጭንቀት ከእኛ አስወግደን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ።