Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 15:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሕዝ​ቡም እጅግ ታወኩ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስ​ንም ተከ​ራ​ከ​ሩ​አ​ቸው፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን፥ ጓደ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አሉት ወደ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሊል​ኳ​ቸው ተማ​ከሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ይህም ጳውሎስንና በርናባስን ከእነርሱ ጋራ ወደ ከረረ ጠብና ክርክር ውስጥ ከተታቸው። ስለዚህ ጳውሎስና በርናባስ ከሌሎች አንዳንድ ምእመናን ጋራ ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው ስለዚሁ ጕዳይ ሐዋርያትንና ሽማግሌዎችን እንዲጠይቁ ተወሰነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውሎና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቆረጠ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ጳውሎስና በርናባስ ስለዚህ ጉዳይ ከሰዎቹ ጋር ንትርክና ክርክር አደረጉ፤ ከዚህ በኋላ ጳውሎስና በርናባስ በአንጾኪያ ካሉ ከሌሎች ጥቂት ወንድሞች ጋር ሆነው ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄዱና ጉዳዩን ለሐዋርያትና ለሽማግሌዎች እንዲያቀርቡ ተወሰነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውሎና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቈረጠ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 15:2
20 Referencias Cruzadas  

ለም​ንም ይሆ​ናሉ ብለን የማ​ና​ስ​ባ​ቸው ናቸው፤ እው​ነ​ተ​ኛው ትም​ህ​ርት በእ​ና​ንተ ይጸና ዘንድ አን​ዲት ሰዓ​ትም እንኳ አል​ተ​ገ​ዛ​ን​ላ​ቸ​ውም።


እኔ ግን ሌሎች ሐዋ​ር​ያት ከአ​ስ​ተ​ማ​ሩት ያጐ​ደ​ል​ሁ​ባ​ችሁ የለም ይመ​ስ​ለ​ኛል።


ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በደ​ረሱ ጊዜም ምእ​መ​ና​ንና ሐዋ​ር​ያት፥ ቀሳ​ው​ስ​ትም ተቀ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ነገ​ሩ​አ​ቸው።


እን​ደ​ዚ​ህም አድ​ር​ገው በበ​ር​ና​ባ​ስና በሳ​ውል እጅ ወደ ቀሳ​ው​ስት ላኩት።


ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሐዋ​ርያ ሊሆን ከተ​ጠራ ከጳ​ው​ሎ​ስና ከወ​ን​ድ​ማ​ችን ከሶ​ስ​ቴ​ንስ፥


በማ​ግ​ሥ​ቱም ጳው​ሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕ​ቆብ ገባ፤ ቀሳ​ው​ስ​ትም ሁሉ በዚያ ነበሩ።


በየ​ከ​ተ​ማ​ውም ሲሔዱ፥ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያዘ​ዙ​ትን ሥር​ዐት አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው።


ይሁ​ዳ​ንና ሲላ​ስን ልከ​ና​ቸ​ዋ​ልና እነ​ርሱ በቃ​ላ​ቸው ይህን ያስ​ረ​ዱ​አ​ች​ኋል።


ሁላ​ችን ከተ​ሰ​በ​ሰ​ብን በኋላ በአ​ንድ ቃል በየን፤ አንድ ሆነ​ንም ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከጳ​ው​ሎ​ስና ከበ​ር​ና​ባስ ጋር ወደ እና​ንተ የም​ን​ል​ካ​ቸ​ውን ሰዎች መረ​ጥን።


መን​ፈስ ቅዱ​ስም፦ ‘ሳት​ጠ​ራ​ጠር አብ​ረ​ሃ​ቸው ሂድ’ አለኝ፤ እነ​ዚህ ስድ​ስቱ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ተከ​ት​ለ​ውኝ መጡና ወደ​ዚያ ሰው ቤት ገባን።


እር​ሱም ተቀ​ብሎ አሳ​ደ​ራ​ቸው፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም ተነ​ሥቶ አብ​ሮ​አ​ቸው ሄደ፤ በኢ​ዮጴ ከተማ ከሚ​ኖ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ችም አብ​ረ​ውት የሄዱ ነበሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን አለው፥ “በእ​ነ​ርሱ ላይ እን​ዳ​ል​ነ​ግሥ እኔን ናቁ እንጂ አን​ተን አል​ና​ቁ​ምና በሚ​ሉህ ነገር ሁሉ የሕ​ዝ​ቡን ቃል ስማ።


ይህ​ንም ቃሌን ብታ​ደ​ርግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ረ​ታ​ሃል፤ መፍ​ረ​ድም ትች​ላ​ለህ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በሰ​ላም ወደ ስፍ​ራው ይመ​ለ​ሳል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios