Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 9:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እኔ ያለ አሳብ እን​ደ​ሚ​ሮጥ ሁሉ እን​ዲሁ አል​ሮ​ጥም፤ ነፋ​ስ​ንም እን​ደ​ሚ​ጐ​ስም ሁሉ እን​ዲሁ አል​ጋ​ደ​ልም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ስለዚህ እኔ ግብ እንደሌለው ሰው በከንቱ አልሮጥም፤ ደግሞም ነፋስን እንደሚጐስም ሰው እንዲያው አልታገልም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ስለዚህ እኔ በከንቱ እንደሚሮጥ እንዲሁ አልሮጥም፤ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እኔ ግን ግብ እንደሌለው ሰው በከንቱ አልሮጥም፤ ነፋስን በቡጢ እንደሚመታ ሰው በከንቱ የምሰነዝር ሰው አይደለሁም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 9:26
17 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።


ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም።


እኔ በሕ​ይ​ወት ብኖ​ርም ክር​ስ​ቶ​ስን ለማ​ገ​ል​ገል ነው፤ ብሞ​ትም ዋጋ አለኝ።


በኀ​ይሉ እን​ደ​ሚ​ረ​ዳኝ እንደ ረድ​ኤቱ መጠን ስለ እርሱ እደ​ክ​ማ​ለሁ፤ እጋ​ደ​ላ​ለ​ሁም።


“ወደ ጠባቡ በር ትገቡ ዘንድ በርቱ፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሊገቡ የሚሹ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ግን አይ​ች​ሉም።


ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፤ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ።


ሰል​ፋ​ችሁ፦ ከጨ​ለማ ገዦች ጋርና ከሰ​ማይ በታች ካሉ ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ንት ጋር ነው እንጂ ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ጋር አይ​ደ​ለ​ምና።


እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤


እን​ግ​ዲህ አን​ፍራ፤ ወደ ዕረ​ፍ​ቱም እን​ድ​ን​ገባ ትእ​ዛ​ዙን አን​ተው፤ ከእ​ና​ን​ተም ምን​አ​ል​ባት በተ​ለ​መደ ስሕ​ተት የሚ​ገ​ኝና የሚ​ጸና ቢኖር ወደ ዕረ​ፍቱ እን​ዲ​ገባ የሚ​ተ​ዉት አይ​ም​ሰ​ለው።


ታም​ነ​ናል፤ ይል​ቁ​ንም ከሥ​ጋ​ችን ተለ​ይ​ተን ወደ ጌታ​ችን እን​ሄ​ዳ​ለ​ንና ደስ ይለ​ናል።


በም​ድር ያለው ማደ​ሪያ ቤታ​ችን ቢፈ​ር​ስም፥ በሰ​ማይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሰው እጅ ያል​ሠ​ራው ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ቤት እን​ዳ​ለን እና​ው​ቃ​ለን።


እን​ዲ​ሁም እና​ንተ በማ​ይ​ታ​ወቅ ቋንቋ ብት​ና​ገሩ፥ ይህ​ን​ኑም ገል​ጣ​ችሁ ባት​ተ​ረ​ጕሙ የም​ት​ሉ​ት​ንና የም​ት​ና​ገ​ሩ​ትን ማን ያው​ቃል? ከነ​ፋስ ጋር እን​ደ​ም​ት​ነ​ጋ​ገሩ ትሆ​ና​ላ​ችሁ።


ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፤ ግፈኞችም ይናጠቋታል።


እንደ ተገ​ለ​ጠ​ል​ኝም ወጣሁ፤ በከ​ንቱ እን​ዳ​ል​ሮጥ፥ ወይም በከ​ንቱ ሮጬ እን​ዳ​ል​ሆነ፥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል የም​ሰ​ብ​ከ​ውን ወን​ጌል አለ​ቆች መስ​ለው ለሚ​ታ​ዩት አስ​ታ​ወ​ቅ​ኋ​ቸው።


መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፤ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፤ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤


እን​ግ​ዲህ እነ​ዚ​ህን የሚ​ያ​ህሉ ምስ​ክ​ሮች እንደ ደመና በዙ​ሪ​ያ​ችን ካሉ​ልን እኛ ደግሞ ሸክ​ምን ሁሉ፥ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ጭን​ቀት ከእኛ አስ​ወ​ግ​ደን፥ በፊ​ታ​ችን ያለ​ውን ሩጫ በት​ዕ​ግ​ሥት እን​ሩጥ።


ይህም ጦር​ነ​ትን ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው ዘንድ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ትው​ልድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ከእ​ነ​ርሱ በፊት የነ​በ​ሩት እነ​ዚ​ህን አላ​ወ​ቋ​ቸ​ውም ነበር፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios